“ርሃብን ለፖለቲካ ዓላማ መጠቀሚያ ማድረግ ተገቢ አይደለም”—-ኮሚሽነር ሺፈራው ተ/ማርያምየአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር ሺፈራው ተ/ማርያም ድርቅን ለፖለቲካዊ ዓላማ መጠቀም “ተገቢ ያ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/mgURWZKktLJj_NSEHZecVVoxf9wbDS0IVH55CiOuJkegIkgSwsDFCCBrSVWFSWGKsuG1qv_Dq6ItSOtO48OYC40H2UYnSlPMLLDCvYMTwEKk9NEgO16sGkup8kE2xcBI52RyfwhoJzaBdPw3h4dOu1lbyLOK5ZbciogDmM8IAAhX01RdBQOSl0AR_jT4jvTiP23pzIvv5LjA7J1XoXtGyO3sA8kpUNvT-4oQne4N1_AEUMuHINqWjbBRQbrugzS6d14P9PGIdUqC-g1UivpJIuL9F4ZIsDr7SLqeS5fKfQ_OUUyIV1qy8MwcWQKi8HtiO9st7NMfB4u1KA9QOCQjvg.jpg

“ርሃብን ለፖለቲካ ዓላማ መጠቀሚያ ማድረግ ተገቢ አይደለም”—-ኮሚሽነር ሺፈራው ተ/ማርያም

የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር ሺፈራው ተ/ማርያም ድርቅን ለፖለቲካዊ ዓላማ መጠቀም “ተገቢ ያልኾነ” እና “ፍጹም ተቀባይነት የሌለው” ድርጊት ነው ብለዋል፡፡

የዓለማቀፍ ተቋማት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅርቡ ያካሄዱት የዳሰሳ ጥናት፣ በኢትዮጵያ ባኹኑ ወቅት የተከሰተው ድርቅ እንጂ ርሃብ እንዳልኾነ ማረጋገጡን ኮሚሽነሩ መግለጻቸውን የኤዜአ ዘገባ ያመለክታል፡፡

ኮሚሽነር ሺፈራው፣ ባኹኑ ወቅት በአገሪቱ 6 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ ፈላጊ እንደኾኑ መግለጣቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

መንግሥት ባለፉት ስድስት ወራት፣ በ11 ቢሊዮን ብር ወጪ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ኩንታል የዕርዳታ እህል ለተረጂዎች ማከፋፈሉን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡

ቀደም ሲል የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የፌደራል መንግስትና የክልሎች የተረጂዎች ቁጥር ሪፖርት በእጅጉ የተለያየ መሆኑ ለእርዳታም አስቸጋሪ እየሆነ እንደሆነ መግለጹ አይዘነጋም፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥር 27 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply