ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ለአንድ የአብን ከፍተኛ አመራር ሹመት ሰጡ።

ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ከፍተኛ አመራር ለሆኑት ለአቶ መልካሙ ፀጋዬ ሹመት ሰጥተዋል። በዚህ መሰረትም አቶ መልካሙ ጸጋዬ የክልሉ ባሕል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሆነው መሾማቸውን በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመለክታል። ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Source: Link to the Post

Leave a Reply