ርዕሰ መስተዳድሩ በሚሰራበት ባጃጅ ውስጥ የተረሳን 35 ሺሕ 900 ብር ለባለቤቱ የመለሰውን ወጣት አመሰገኑ

አርብ ነሐሴ 6 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በሚሰራበት ባጃጅ ውስጥ የተረሳን 35 ሺሕ 900 ብር ለባለቤቱ ለመለሰው ወጣት ምስጋና አቅርበዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በሚሰራበት ባጃጅ ውስጥ በተሳፋሪ የተረሳን 35 ሺሕ 900 ብር ለባለቤቱ የመለሰውን ወጣት አብዱሰላም ሀሰን በፅ/ቤታቸው ላከናወነው መልካም ተግባርም ምስጋና አቅርበውለታል።

በወቅቱም እንዲህ ለወገን የሚቆረቆሩ መልካም ሥነምግባር ያላቸው ወጣቶች ለአገር ያስፈልጋሉ ብለዋል፡፡

ወጣት አብዲሰላም ሀሰን የሰራው መልካም ተግባር ሌሎች ወጣቶች መውሰድ እንዳለባቸውም በመግለጽ፤ የክልሉ መንግስት ለወጣቱ እገዛ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply