ሮናልዶ በኮቪድ 19 ተያዘ።የፖርቱጋል እና ጁቬንቱስ አጥቂ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ በኮሮና ቫይረስ መያዙ ተረጋገጠ፡፡ ይህንን ያለው የፖርቱጋል እግር ኳስ ፌደሬሽን ነው፡፡ የ35 ዓመቱ ተጫዋች ምን…

ሮናልዶ በኮቪድ 19 ተያዘ።

የፖርቱጋል እና ጁቬንቱስ አጥቂ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ በኮሮና ቫይረስ መያዙ ተረጋገጠ፡፡

ይህንን ያለው የፖርቱጋል እግር ኳስ ፌደሬሽን ነው፡፡

የ35 ዓመቱ ተጫዋች ምንም ዓይነት ምልክት ያላሳየ ሲሆን ራሱን አግልሎ እንዲቆይ ወደ ከብሄራዊ ቡድኑ ወደ ቤቱ ተመልሷል፡፡

ፖርቱጋል ነገ ምሽት በኔሽንስ ሊግ ጨዋታ ስዊዲንን ትገጥማለች፡፡

የፈርናንዶ ሳንቶስ የፖርቱጋል ብሄራዊ ቡድን ቀሪዎቹ አባላት በሙሉ ከኮቪድ ነጻ መሆናቸው ተነግሯል፡፡

ባሳለፍነው እሁድ ከፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን ጋር 0ለ0 የተለያየው የፖርቱጋል ብሄራዊ ቡድን ከዓለም ሸምፒዮኖቹ ጋር በነጥብ እኩል ቢሆኑም ምድባቸውን በበላይነት እየመሩ ይገኛሉ፡፡

በአቤል ጀቤሳ
ጥቅምት 3 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply