ሰላማዊ ምርጫ እንዲከናውን የምርጫ ጣቢያዎች ላይ አስፈላጊውን የፀጥታ ሀይሎች መደበው እየሰሩ መሆናቸውን ክልሎች ገለፁ፡፡

የሀረሪ ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሄኖክ ሙሉነህ ለአሀዱ እንዳሉት 6ተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ ነው፡፡

እስካሁን በክልሉ የሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ምንም አይነት ችግሮች እንዳላጋጠማቸው ያነሱት አቶ ሄኖክ  ሰላማዊ ምርጫ እንዲከናወንም የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ተጨማሪ የፌደራል ፖሊስ በየደረጃው የሚገኙ የፀጥታ አካላት የጋራ እቅድ አውጥተው እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ድእስካሁን ድረስ በክልሉ ሀገራዊ ምርጫን ለማደናቀፍ የሚስችሉ ጥቃቶችና ግጭቶች የሌሉ ሲሆን በቀጣይም ምርጫ ጣቢያዎች ላይ ችግሮች እንዳይጋጥሙ የክልሉ መደበኛ ፖሊስ ፣ሚሊሻ እና የፌደራል ፖሊስ ተቀናጅተው በጋራ እየሰሩ መሆናቸውን ያነሱት ደግሞ የጋምቤላ ክልል ሰላምና ደህንነት ቢሮ ሃላፊ አቶው ኦኮት ናቸው፡፡

በተጨማሪ እካሁን የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ችግሮች እንዳላጋጠማቸው እና በቀጣይ ምርጫው በሰላማዊ መንገድ እንዲከናወን በክልሉ የሚገኙ የፀጥታ ሃይሎችን አቀናጅተው እየሰሩ መሆናቸውን የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ መለሰ ሙሉነህ ገልፀዋል፡፡

ቀን 23/09/2019

አሐዱ ራድዮ 94.3

The post ሰላማዊ ምርጫ እንዲከናውን የምርጫ ጣቢያዎች ላይ አስፈላጊውን የፀጥታ ሀይሎች መደበው እየሰሩ መሆናቸውን ክልሎች ገለፁ፡፡ appeared first on አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን.

Source: Link to the Post

Leave a Reply