“ሰላም ይስፈን በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚደርስ ጥቃት ይቁም” በሚል መሪቃል ነገ ታህሳስ 10 ቀን 2014 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ ህዝባዊ ሰልፍ እንደሚካሄድ የአዲስ አበበ ፖሊስ አስታወቀ…

“ሰላም ይስፈን በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚደርስ ጥቃት ይቁም” በሚል መሪቃል ነገ ታህሳስ 10 ቀን 2014 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ ህዝባዊ ሰልፍ እንደሚካሄድ የአዲስ አበበ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
“የእህቴ ጠባቂ ነኝ” በሚል መልዕክት ነገ ታህሳስ 10 ቀን 2014 ዓ/ም የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት እና በርካታ ህዝብ የሚታደምበት “ሰላም ይስፈን በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚደርስ ጥቃት ይቁም” በሚል መሪቃል በመስቀል አደባባይ ህዝባዊ ሰልፍ እንደሚካሄድ የአዲስ አበበ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
በአማራና በአፋር ክልሎች አሸባሪው የህወሃት ጁንታ በፈፀመው ግጭት በርካታ ህዝብ የተፈናቀለ ሲሆን በሴቶችና በህፃናት ላይ እየተፈፀመ ያሉ ጥቃቶች እንዲሁም እየደረሰ ያለውን የንብረት ውድመት የምዕራቡ ዓለምና የእነሱን አጀንዳ የሚያራምዱ ሚዲያዎች በዝምታ በማለፋቸው እንዲሁም አገራችን በምታካሂደው የሰላም ማስከበር ስራ ላይ ጣልቃ እየገቡ በመሆኑ ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ለሰላም ወዳድ አካላት መልዕክት ለማስተላለፍ ሰልፉ እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡
በመሆኑም ነገ ታህሳስ 10 ቀን 2014 ዓ/ም መረሃ ግብሩ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል። በዚህም መሰረት
• ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን ላይ እና ታች መንገዶች
• ከቦሌ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ ላይ እና ታች መንገዶች
• ከ4 ኪሎ በውጪ ጉዳይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሄራዊ- ቤተ መንግስት
• ከአዋሬ ካዛንቺስ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ካዛንቺስ መብራት
• ከሜክሲኮ፣ለገሃር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለገሃር ትራፊክ መብራት ላይ
• ከሰንጋ ተራ ብሄራዊ ቴአትር ስታዲዮም የሚወስደው መንገድ ንግድ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት
• በቸርችል ጎዳና ፖስታ ቤት፣ ሃራምቤ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሐራምቤ መብራት
• ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ እና ለቀላል ተሸከርካሪ ጥላሁን አደባባይ ዝግ የሚሆን ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ከዛሬ ምሽት 12 ሰዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ ዙሪያ እና በእነዚህ መንገዶች ላይ ተሽከርካሪን ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል።
አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም የተለመደ ትብብራቸውን እንዲያደርጉ የጠየቀው የአዲስ አበባ ፖሊስ በተለይም ወቅታዊውን የሀገራችንን የፀጥታ ሁኔታ ከግምት በማስገባት ሰላም ወዳድ የከተማችን ነዋሪዎች እንደሁልጊዜውም የከተማችንን ሰላም ለማስጠበቅ ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ መልዕክቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ መልእክቱን አስተላልፏል ፡፡
ታህሳስ 09 ቀን፣ 2014 ዓ.ም
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን

Source: Link to the Post

Leave a Reply