ሰልፉን በተመለከተ ኢህአፓ ምን አለ?ሰልፉ አልተሰረዘም ሀሰተኛ መረጃ ነው ብሏል ኢህአፓ፡፡በማህበራዊ ሚዲያዎች የህዳር 30 ሰልፍ እንተሰረዘ በማድረግ የሚናፈሰው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን የኢትዮ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/GYIbZt50kjaON6U23b5jPboQcR-GdT0CEzAGiFv8s0i56TlLri-C6AD6V8ChfSKFdNnxMsqy1XhN4oHrlE5je4_GqV8o7zSmtOphARWEn7E8yPwYQ7r9snd3BDsfqFckzZ-aFEiDMiMpBFPwoIPUFxttKmJT1O8A2TQ510aIxdecBJ5vz4z2Sw_38FQpFs9BHXivatQXuQRdDvTUMH8ryKl7iBTMfe1CYEtV8uyWBQPLBOOrNt2m0hzxKfsooHUWKh0b8v1FaQnjirAp6ZJl0fct1-O7lQEVSOE75WhHLqdGBDlNgJ5Z-T3AKCOiP6DwbzyUTNe6AIoNNFQoP8GdlA.jpg

ሰልፉን በተመለከተ ኢህአፓ ምን አለ?

ሰልፉ አልተሰረዘም ሀሰተኛ መረጃ ነው ብሏል ኢህአፓ፡፡

በማህበራዊ ሚዲያዎች የህዳር 30 ሰልፍ እንተሰረዘ በማድረግ የሚናፈሰው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ ኢህአፓ አስታውቋል፡፡

በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተቀባበሉት ያለው የሰልፍ መሰረዝ መረጃ ፍፁም ሀሰት ነው ሲሉ የኢህአፓ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር መጋቢ ብሉይ አብርሃም ሀይማኖት ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ይህን መረጃ በተመለከተ በኢህአፓ ዕውቅና ባለው የፌስ ቡክ ገፅም ሆነ በቴሌግራም ገፁ ያልተገለፀ ኢህአፓ የማያውቀው መሆኑ ሊታወቅ ይገባል ሲሉ ለጣብያችን ተናግረዋል፡፡

ኢህአፓ እንደ ስራ አስፈፃሚ ሰልፉን ይደግፈዋል ሙሉ ድጋፉንም ይሰጣል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

እሁድ ህዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ለማድረግ እቅድ እንደተያዘለት የሚነገረውና መንግስት እውቅና እንደነፈገው የሚገለጸው ሰላማዊ ሰልፍ አራት ኪሎ ከሚገኘው የድል ሐውልት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ የሚጠናቀቅ መሆኑ በአስተባባሪዎቹ መገለጹ አይዘነጋም፡፡

በአቤል ደጀኔ

ህዳር 26 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply