
በሰሜን ኢትዮጵያ ላለው ችግር በአፍሪካ ኅብረት በኩል የሰላማዊ መፍትሔ አማራጮች እንዲታዩ ገዢው የብልጽግና ፓርቲ ውሳኔ ማሳለፉን የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ተናገሩ። ብልጽግና ፓርቲ ባለፈው ሳምንት ማብቂያ፣ የሥራ አስፈጻሚና የማዕከላዊ ኮሚቴዎቹን ስብሰባ ማድረጉን ተከትሎ በተሰጠው መግለጫ በሰሜን ኢትዮጵያ ስላለው ጦርነት እና በሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መክሮ ውሳኔ ማሳለፉ ተገልጿል።
Source: Link to the Post