ሰሜን ኮሪያ በዛሬው ዕለት በምሥራቅ የባሕር ዳርቻዋ አካባቢ በርከት ያሉ ቦለስቲክ ሚሳኤሎችን ተኮሰች።

የደቡብ ኮሪያ የመከላከያ ባለሥልጣናትም ሚሳኤሎቹ ከተጠቀሰው አካባቢ መተኮሱን አረጋግጠዋል።

ሰሜን ኮርያ የመከላከያ ስልት አቋሟን የማሳደጊያ መርሐ ግብር አካል ነው በሚል በቅርብ ወራት ክሩዝና ቦለስቲክ ሚሳኤሎችን ጨምሮ ስልታዊ ሮኬቶችን ተኩሳለች።

የፕሬዝደንት ኪም ጆን ኡን እህት ዛሬ ማለዳ ሀገራቸው የደቡብ ኮርያን ወታደራዊ ወረራ ለማክሸፍ ሚሳኤሎቹን መተኮሷን አረጋግጠዋል።

አሜሪካ እና ደቡብ ኮርያ የፒዮንግያንግን መንግሥት ለሩሲያ የጦር መሣሪያ በመላክ ይከሳሉ፤ የሰሜን ኮርያ መንግሥት ግን ክሱን ውድቅ ያደርጋል።

ሰሜን ኮርያ ዛሬ ሚሳኤል ስትተኩስ የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን በቻይና ሰሜን ምሥራቅ ግዛት ሀርቢን ጉብኝት እያደረጉ ነው።

ፑቲን እና የቻይናው ፕሬዝደንት ሺ ጂምፒንግ ዋሽንግተን እና ተባባሪዎቿ በሰሜን ኮርያ ላይ የበጦር መሣሪያ እያስፈራሩ ነው በሚል ይተቻሉ።

ግንቦት 9 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply