ሰሜን ኮርያ የሚሳይል ፍተሻ ተኩስ አካሄደች

https://gdb.voanews.com/01bd0000-0aff-0242-ac73-08d9f9ebef38_w800_h450.jpg

ሰሜን ኮሪያ በቤይጂንግ የሚካሄደው የክረምት ኦሎምፒክስ ከተጀመረ ወዲህ ለአንድ ወር ገደማ አቋርጣ የነበረውን የቦለስቲክ ሚሳይል ተኩስ ዛሬ ጠዋት አካሂዳለች። 

ደቡብ ኮርያ ለጋዜጠኞች ባለተላለፈችው መልዕክት፣ ሰሜን ኮሪያ ከጠዋቱ አንድ 1ሰዓት ከ 52 ደቂቃ ላይ የተኮሰችው ሚሳይል ከሱናን አካባቢ ተነስቶ  በፔኔንሱላ ምስራቃዊ የባህርዳር ዳርቻ አቅራቢያ የሚገኝ ውሃ ውስጥ አርፏል። 

ይህን ተከትሎ በሲኦል የሚገኘው ብሄራዊ የፀጥታ ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ በፕሬዝዳንቱ ፅህፈት ቤት ያካሄደ ሲሆን፣ ባለስልጣናቱ ዓለም በዩክሬን እየተካሄደ ያለውን ጦርነት ለማስቆም ጥረት እያደረገ ባለበት ወቅት የሚሳይል ፍተሻ ተኩስ መካሄዱ በከፍተኛ ሁኔታ እንዳሳሰባቸው አስታውቀዋል። 

የዩናይትድ ስቴትስና የህንድ ፓስፊክ ዕዝ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ሰሜን ኮሪያ ያካሄደቸውን የቦለስቲክ ሚሳይል ተኩስ አውግዞ ፒዮንግያንግ ከተጨማሪ አዋኪ ድርጊቶች እንድትቆጠብ አስጠንቋል። በጉዳዩ ላይ ከደቡብ ኮሪያ፣ ጃፓን እና ሌሎች የቀጠናው አጋሮች ጋር እየተነጋገረ መሆኑንም ጨምሮ ገልጿል። 

Source: Link to the Post

Leave a Reply