You are currently viewing ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት በድሬሮቃ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የ100 ሺህ ብር ድጋፍ አደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ    መጋቢት 9 ቀን 2015 ዓ/ም          አዲስ አበባ ሸዋ ብፁዕ አቡ…

ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት በድሬሮቃ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የ100 ሺህ ብር ድጋፍ አደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 9 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ብፁዕ አቡ…

ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት በድሬሮቃ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የ100 ሺህ ብር ድጋፍ አደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 9 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ (የክብር ዶ/ር) የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች ተፈናቅለው በድሬሮቃ (ጃራ መጠለያ ጣቢያ) የሚገኙ ወገኖችን ጎብኝተዋል። በጉብኝታቸው ወቅት ሀገረ ስብከቱ የ100 ሽህ ብርና የጫማ ድጋፍ ማድረጉን የገለፁት ብፁዕነታቸው ሽማግሌዎች፣ እናቶችና ሕፃናት በከፋ አኗኗር ውስጥ በመሆናቸው በጎ አድራጊዎችና ለጋሽ ድርጅቶች አስቸኳይ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪም አቅርበዋል። በጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ የሚገኙ ዜጎች አኗኗራቸው ልብ ሰባሪ በመሆኑ መንግሥት፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና የማኅበረሰብ አንቂዎች ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም አባታዊ መልእክት አስተላልፈዋል። ከተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ተፈናቅለው በሰሜን ወሎ ዞን ብቻ 47 ሺህ ወገኖች በጊዜያዊ መጠለያ እንደሚኖሩና ከዚህ ውስጥ ድሬሮቃ (ጃራ) መጠለያ ጣቢያ የሚገኙት 10 ሺህ መሆናቸውን ከዞኑ ምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። ምንጭ_የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት

Source: Link to the Post

Leave a Reply