“ሰሞኑን ከአዲስ አበባ ዙሪያ ቤቷ ፈርሶባት ልጆቿን አንጠልጥላ ወደ ደብረማርቆስ የመጣች አንዲት ነፍሰ ጡር የነገረችኝ!…” የጤና ባለሙያ የሆነው የስነ ቃል ወርቁ ትዝብት! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … የካቲት 22 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ዛሬ ቀን ነፍሰ ጡር እናቶችን የቅድመ ወሊድ ምርመራ እያደረኩ ነበር። አንዲት እናት ተራዋ ደርሶ ስሟ ተጠርቶ ገባችና ተቀመጠች። አንድአንድ መጠይቆችን ባነሳሁ ጊዜ ይህች እናት የ3 ልጆች እናት እንዲሁም አራተኛ ደግሞ ነፍሰ ጡር እንደሆነች እና ሰሞኑን ከአዲስ አበባ ዙሪያ ቤቷ ፈርሶባት ልጆቿን አንጠልጥላ ወደ ደብረማርቆስ የመጣች መሆኗን ነገረችኝ። ሌላም ነገር እንዲህ ስትል ነገረችኝ:_” እንደ እኛ ቤታቸው የፈረሰባቸው የደቡብ ክልል ሰዎች ነበሩ ነገር ግን እነሱ ” መንግስታቸው ወዲያውኑ 200 ካሬ መሬት እየሸነሸነ ነው የተቀበላቸው። እኛ ግን በየት ወደቁ የሚለን የለም። አለችኝ። ለካ ይሄም ልዩነት አለ ?? ብየ እጅግ አዝኜ ብሶቷን ሁሉ አዳመጥኳት። ምን ያደርጋል? ባዶ ማዳመጥ ነው እንጂ አዳመጥኳት!!
Source: Link to the Post