ሰራተኛዋ እራሷን ለአደጋ አጋልጣ አካባቢውን ከእሳት ታደገች።

በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሁለት በተለምዶ ጣሊያን ሰፍር በአንድ ምግብ ቤት ሊፈነዳ የነበረ ሲሊንደር ከቤቱ በማውጣት በሰው እና በንብረት የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ አድርጋለች።

በአካባቢው የነበሩት ወጣቶች የሰራተኛዋ ጥሪ ተቀብለው የድንገተኛ አደጋ ተቆጣጣሪዎች እስኪደርሱ ድረስ ሲሊንደሩ የከፋ ጉዳት እንደያደርስ አፈር በማድረግ የተቻላቸውን አድርገዋል።

ከባልደረባችን ሔኖክ ወ/ገብርኤል ስልክ የደረሳቸው የእሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ሰራተኞች በቦታው በፍጥነት በመድረስ ፎም እና ውሀ በመርጨት ሲሊንደሩን ማጥፋት ችለዋል።

ሲሊንደሩን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ከአንድ ሰአት በላይ መፍጀቱን ጣበያችን አረጋግጧል።

ሰራተኛዋ ሲሊንደሩን ከምግብ ቤቱ ባታስወጣው ኖሮ ለመቆጣጠር የሚያዳግት አደጋ ይደርስ እንደነበረ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ተናግረዋል።

ሰራተኛዋ የራሷን ህይወት ለአደጋ አጋልጣ የሰው እና የንብረት ውድመት መታደጓን ባለሙያዎቹ ገልጸዋል።

በሰራተኛ ላይ የደረሰ የጉዳት ምልክት አለመኖሩን አረጋግጠናል።

የአካባቢው ነዋሪዎችም ሰራተኛዋ ባደረገችው ድርጊት ተገርመው አድናቆት ችረዋታል።

በዚሁ አጋጣሚ ምግብ ቤቶች ሲሊንደር ሲጠቀሙ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እና ሰራተኞቻቸው አጠቃቀሙን እንዲያውቁ ስልጠና መስጠት እንዳለባቸው ነው በስፍራው የተገኙ ባለሙያዎች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

መጋቢት 02 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply