ሰራዊቱ በሰፈረባቸዉ ካምፖች የተከፈተበትን የከሃዲዎች ጥቃት በብቃት መክቶ ወደ ጸረ ማጥቃት እርምጃ ተሸጋግሯል- መከላከያ ሚኒስቴር

ሰራዊቱ በሰፈረባቸዉ ካምፖች የተከፈተበትን የከሃዲዎች ጥቃት በብቃት መክቶ ወደ ጸረ ማጥቃት እርምጃ ተሸጋግሯል- መከላከያ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 25 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሰራዊቱ በሰፈረባቸዉ ካምፖች የተከፈተበትን የከሃዲዎች ጥቃት በብቃት መክቶ ወደ ጸረ ማጥቃት እርምጃ መሸጋገሩን የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሰራዊቱ ተኩስ በተከፈተበት ካምፖች ሁሉ በጠንካራ መከላከል ውጊያ የከሃዲውን ሃይል በጀግንነት መክቶ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰበት ይገኛል፡፡
የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊትና የአማራ የጸጥታ ሃይል ተቀናጅተዉ በሰሜን ጎንደር ዞን ቀራቅር በተባለ ቦታ የእብሪተኛዉ ቡድን የሰነዘረዉን የማጥቃት ውጊያ በብቃት በመመከት በዚህ ሃይል ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊና ማቴሪያላዊ ኪሳራ አድርሶበታል፡፡
ሰራዊቱ በዛሬዉ እለት ከሰዓት በኋላ በወሰደዉ ቅንጅታዊ የማጥቃት እርምጃ ከቀራቅር በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘዉ ከፍተኛ ቦታ ላይ የነበረዉን የእብሪተኛዉ አጥፊ ቡድን ሃይል በከፍተኛ ሁኔታ በማጥቃት ቦታዉን ቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታውቋል።
ጀግናዉ ሰራዊት በወሰደዉ የማጥቃት እርምጃ በዚህ ነብሰ በላ ቡድን ሃይል ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊ ኪሳራ በማድረስ የቡድንና የነብስ ወከፍ መሳሪያዎችንም ማርኳል ፡፡

The post ሰራዊቱ በሰፈረባቸዉ ካምፖች የተከፈተበትን የከሃዲዎች ጥቃት በብቃት መክቶ ወደ ጸረ ማጥቃት እርምጃ ተሸጋግሯል- መከላከያ ሚኒስቴር appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply