ሰበር!
ህወሓት ከሽብርተኛ ድርጅትነት ተሰረዘ።
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከሽብርተኛ ድርጅት እንዲሠረዝ ውሳኔ አሳለፈ፡፡
ምክር ቤቱ ዛሬ ባሄደው ልዩ ስብሰባ ህወሓትን ከሽብርተኛ መዝገብ ለማንሳት በቀረበለት የውሳኔ ሀሳብ ላይ ከተወያየ በኋላ በአብላጫ ድምፅ ውሳኔውን አፅድቋል።
በዛሬው ልዩ ጉባኤ 280 የፓርላማ አባላት ተገኝተው ነበር፡፡
በዚህ ልዩ ጉባኤ የህወሓት ከሽብርተኝነት መሰረዝ 61 የፓርላማ አባላት ተቃውመውታል፤አምስት የፓርላማ አባላት ደግሞ ድምጽ ከመስጠት ታቅበዋል።
በዚህም መሰረት ህወሃትን ከሽብርተኝነት የማንሳት ወይም ያለማንሳት “ልዩ ጉባኤ” በአብላጫ ድምጽ ህወሃት ከሽብርተኝነት ዝርዝር እንዲነሳ ተወስኗል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መጋቢት 13 ቀን 2015 ዓ.ም
ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ!
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን