ሰበር መረጃ ለሚመለከተው ሁሉ ነሐሴ 22/2014 ዓ.ም (አሻራ ሚዲያ) የታሪካዊ ጠላትችን አንዱ አካል የሆነው ኦነግ ሸኔ በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ውስጥ ኪሚሴ ከተማ አካባቢ ባሉ ቀጠናዎች ጦርነ…

ሰበር መረጃ ለሚመለከተው ሁሉ ነሐሴ 22/2014 ዓ.ም (አሻራ ሚዲያ) የታሪካዊ ጠላትችን አንዱ አካል የሆነው ኦነግ ሸኔ በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ውስጥ ኪሚሴ ከተማ አካባቢ ባሉ ቀጠናዎች ጦርነት ለመክፈት እንቅስቃሴ ላይ መሆኑ ተደርሶበታል። ስለሆነ ሸዋ እና አካባቢው እንዲሁም ይፋት ቀጠና የጥንቃቄ ስራዎች ሊሰራ ይገባል። የሰሜን ሸዋ ይፋት ቀጠና አካባቢ የተለየ ትኩረት እንዲሰጠው እያሳሰብን መንግስት አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ የፀጥታ ሃይል አካባቢው ላይ እንዲያጠናክር ይሁን እላለሁ። በሰሜን ሸዋ አካባቢ ያላችሁ የፀጥታ ሃይሎች እና የፋኖ አስተባባሪዎች በሸዋሮቢት እና አካባቢው፣በይፋት እና አካባቢው፣ አጣየ እና አካባቢው እንድሁም ምንጃር እና አካባቢው የጥንቃቄ ስራዎችን በመስራት አስፈላጊውን ዝግጅት እንድደረግ ለማሳሰብ እወዳለሁ። ከራያ ቆቦ እና አካባቢው ከፍተኛ ሺንፈት የደረሰበት ወያኔ በጎን በኩል የሃይል ሚዛኑን ለማዛባት ሰሜን ሸዋ አካባቢን የማተራመስ እንቅስቃሴ እየተካሄደ እንዳለ መረጃዎች ያሳያሉ። ስለሆነም ጥንቃቄ የሁሉም ነገሮች አሸናፊ እስከሆነ ድረስ የአካባቢው መስተዳድር እና የፀጥታ አካላት አስፈላጊውን ትኩረት እንድታደርጉ አማራዊ ጥሪያችንን እናስተላልፈለን። ያልጠረጠረ ተመነጠረ እንደሚባለው በሁሉም አቅጣጫ ሃላፊነት የተሞላበት እንቅስቃሴ እናድርግ!! ትኩረት ለሸዋ ቀጠና!! እናሸንፋለን!! © አሸናፊ ገናን ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply