#ሰበር መረጃ በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ኦነግ ሸኔ በከፈተው ጥቃት ከ80 በላይ ንፁሃን መገደላቸው ተሰማ አሻራ ሚዲያ … ሰሜን አሜሪካ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ…

#ሰበር መረጃ በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ኦነግ ሸኔ በከፈተው ጥቃት ከ80 በላይ ንፁሃን መገደላቸው ተሰማ አሻራ ሚዲያ … ሰሜን አሜሪካ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ የኦነግ ሸኔ ሃይሎች ዛሬ ከረፋዱ ሦስት ሰዓት ጀምሮ በከፈቱት ጥቃት ከ80 በላይ ንፁኋኖች መገደላቸውን የአከባቢው ነዋሪዎች ለአማራ ድምፅ ተናግረዋል። በቶሌ ቀበሌ ልዩ ስሙ ጃተማ በተባለ ቀበሌ አከባቢ ዛሬ ከሦስት ሰዓት ጀምሮ ታጣቂዎቹ በከፈቱት ጥቃት ከ 80 በላይ የሚሆኑ የአማራ ተወላጆች መገደላቸውን ነው ነዋሪዎቹ ያረጋገጡት። ከአማራ ድምፅ ጋር የስልክ ቆይታ ያደረጉት ነዋሪዎቹ ከተገደሉት መካከል ሴት እና ህፃናት ይበዛሉ ያሉ ሲሆን ለወረዳ እና ለዞን አመራሮች ቢያመለክቱም ነገር ግን ሊደርሱላቸው እንዳልቻሉ ገልፀዋል። ከጥቃቱ የተረፉት ህይወታቸውን ለማትረፍ ወደ ጫካ መሸሻቸውን የሚናገሩት ነዋሪዎቹ የመንግስት የፀጥታ ሃይሎች ገብተው እንዲታደጓቸው ተማፅኖ አቅርበዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply