#ሰበር መረጃ # በጎጃም ቢቡኝ የ13 ዓመትን ልጅ “ፋኖ ነህ” ተብሎ በጥይት ተገደለ!! ሰ.አሜሪካ:- ግንቦት 18/2014 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ # በአካባቢ…

#ሰበር መረጃ # በጎጃም ቢቡኝ የ13 ዓመትን ልጅ “ፋኖ ነህ” ተብሎ በጥይት ተገደለ!! ሰ.አሜሪካ:- ግንቦት 18/2014 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ # በአካባቢው ፋኖ አወቀ መንጌም ተገድሏል! / ፋኖን ትጥቅ ለማስፈታት በምስራቅ ጎጃም ዞን፤ ቢቡኝ ወረዳ፤ የወይን ውሃ ከተማ አቅራቢያ፣ የ13 ዓመት አዳጊ ልጅን ከትናንት በስቲያ ማክሰኞ ግንቦት 16 ቀን 2014 ዓ.ም. ተገድሏል። “ፋኖ ነህ” በሚል በ3 ጥይት ተደጋግሞ ቤት ውስጥ በመደብደብ ነበር ሕፃኑ የተገደለው። ሟቹ የ4ኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን በወቅቱ ከብቶችን እየጠበቀ ነበር። በተመሳሳይ፣ በዚያው በቢቡኝ ፋኖ አወቀ መንጌ ከሕፃኑ መሰዋዕት ጥቂት ደቂቃዎች ቀደም ብሎ በፖሊስ ተገድሏል። ይህ ግድያ በሜዳ ላይ ሲፈፀም የተመለከተው ሕፃን ድርጊቱን ለመናገር ሩጦ ወደ ቤት ሄዷል። ይህን ተከትሎ፣ ታጣቂዎቹ በጥይት ተኩስ እያባረሩ ተከትለውት ከቤት ገብተዋል። ቤት ውስጥም ደጋግመው በቤተሰብ አባላትና በጎረቤት ፊት በጥይት በመደብደብ ገድለውታል። አስክሬኑን ጎትተው ከቤት አውጥተው በር ላይ በመጣል “ተባራሪ ጥይት ገደለው በሉ” የሚል ማስጠንቀቂያ ተናግረው እንደሄዱ የቤተሰቡ አባላት ገልፀዋል። የፋኖ አወቀ መንጌ እና የሕፃን ልንገረው አዲስ የቀብር ስነ ስርዓት በዚያው በተሰውበት ዕለት፤ በተገደሉበት ስፍራ ማለትም በቢቡኝ ወረዳ፤ በደብረ ሲና አስማረ ቀበሌ፤ በጋፋት ሚካኤል ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል። ዘገባው—-ሰሜን አሜሪካ ባልደራስ

Source: Link to the Post

Leave a Reply