ሰበር መረጃ ከ900 በላይ አማሮች ከኦሮሚያ ክልል ም/ ወለጋ ተፈናቅለው አማራ ክልል ገቡ። /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 20/2013ዓ.ም ባህርዳር ///… ባለፈው ጥቅምት 4/2013ዓ.ም…

ሰበር መረጃ ከ900 በላይ አማሮች ከኦሮሚያ ክልል ም/ ወለጋ ተፈናቅለው አማራ ክልል ገቡ። /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 20/2013ዓ.ም ባህርዳር ///… ባለፈው ጥቅምት 4/2013ዓ.ም ጀምሮ በምዕ/ወለጋ ሆሮጉዱሩ ዞን በኦነግ ታጣቂዎች የሚኖሩ አማሮች ላይ ጦርነት ከፍቶ በርካቶችን መግደሉ እና ሀብት ንብረታቸውን መዘረፋቸውን መግለፃችን ይታወሳል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ከትናንት ጀምሮ 20 አማሮች በወለጋ አካባቢ በኦነግ ሸኔ ወታደሮች ታግተው እንደሚገኙ ከቦታው ያሉ የመረጃ ምንጫችን አድርሰውናል። በሌላ በኩል ከኦሮሚያ ክልል ወለጋ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ከ900 በላይ አማሮች በዛሬው እለት ጥቅምት 20/2013 ዓ.ም ምስራቅ ጎጃም ጉምደወይን ገብተዋል።የአካባቢው ወጣቶች ጊዜያዊ ምግብ አቅርቦት እያቀረቡላቸው እንደሆነ ለማወቅ ችለናል። ተጨማሪ መረጃዎችን ይዘን እናቀርባለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply