
ሰበር መረጃ ዛሬ በቡራዩ ማርያም ቤተክርስቲያን ጥቁር ልብስ ለበሳችሁ በሚል በኦሮሚያ ፖሊስ በርካታ ምዕመናን ክፉኛ ድብደባና የግፍ እስራት ተፈፅሟል ሲሉ ለአሻራ ምንጮች ገለፁ! ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ #በቡራዩ ማሪያም ቤተክርስቲያን ምዕመናን ላይ ከፍተኛ ድብደባ እና የግፍ እስር ተፈፀመ። በቡራዩ ማሪያም ቤተክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶሱን ትዕዛዝ ተቀብለው ጥቁር ልብስ በለበሱ በርካታ ምመኖች ላይ የኦሮሚያ ፖሊስ ከፍተኛ ድብደባ የፈፀመ ሲሆን በርካቶቹን በግፍ ማሰሩ ታውቋል። ዛሬ ጥር 29/2015 ዓ/ም ህገወጡን ቡድን እየደገፉ የሚገኙት የስርዓቲ አገልጋይ ወታደሮች የአባቶችን ትዕዛዝ በተቀበሉ ህዝበ ክርስቲያኖች ላይ ከፍተኛ የሆነ ድብደባ፣እስራት እና ወከባ ሲፈፅሙ መዋላቸው ተረጋግጧል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post