
ሰበር መረጃ የነ እስክንድር ነጋ ችሎት ለአራት ወራት መቀጠር አስመልክቶ ችሎት ውስጥ ከፍተኛ መካረር ተነሳ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ 16/2013 ዓ•ም ባህር ዳር የነ አስክንድር ቀጥሮ መጋቢት 29 መሆኑን ተከተሎ ነው ብጥብጥ የተነሳው። ችሎቱን ለመከታተል ወደ/ፍ/ቤት ያቀናው የአዲስ አበባ ወጣት ነው በቁጣ ድምፁን ያሰማው። ምስክር ለማሰማት በሚል ፍ/ቤቱ መጋቢት 29 ቀን ከአራት ወር በኋላ መቅጠሩን ተከትሎ ነው ወጣቶቹ ከፍተኛ ብስጭት ውስጥ የገቡት። ችሎት ሊከታተል የገባውን የአዲስ አበባ ወጣት ቀጠሮውን ተከትሎ ዳኞችና እነ እስክንድር መካረር ውስጥ በመግባታቸው ወጣቱ በፖሊስ ተገዶ እንዲወጣ ተደርጓል ሲል ባልደራስ ለእውነተኛ ድሞክራሲ በማህበራዊ ገፁ አስፍሯል።
Source: Link to the Post