ሰበር መረጃ: የአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤት ተመሰረተ! ሕዳር 16 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር ከአማራ ፋኖ አንድነት የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ:- የሁሉም ህዝባችን ጥያቄ…

ሰበር መረጃ: የአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤት ተመሰረተ! ሕዳር 16 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር ከአማራ ፋኖ አንድነት የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ:- የሁሉም ህዝባችን ጥያቄ እና ፍላጎት የነበረዉ የፋኖ አንድነት የአማራ ፋኖ አንድነት በሚል ስያሜ ተቋቋመ:: ስለሆነም የአማራ ፋኖ አንድነት ህዳር 13/2015 ዓ.ም ጎንደር ላይ ከሁሉም ክፍል ሀገራት በተወጣጣ ሀይል ማለትም ከጎንደር ፣ከወሎ ፣ከሽዋ እና ከጎጃም ምክርቤቱ የተመሰረተው ምስራቅ አማራ ፋኖ+የአማራፋኖ ህብረት በጎንደር+የአማራ ሕዝባዊ ኃይል ፋኖ +የሸዋ ፋኖ እና የባህርዳር ፋኖ በተወጣጣ ሀይል በዛሬ ዕለት የአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤት ተመስርቷ፡፡ ለዚህ ስኬት በቅንነት ስተሰሩ ለነበራቹ አማራዎች እና የአማራ ሞት ፣መሰደደ ፣መገላታት ያገባናል የሚትሉ ወዳጆቻችን እንኳን ደስ አላቹህ:: ከሁሉም በላይ ትጥቅ፣ ስንቅ፣ ጫካ እና ምሽግ ለሆናቹህን በውስጥና በወጭም ያላቹ አማራዎች እንካን ደስ አላቹ!! ፍኖነት በጠብታ ውሀ እየተዋለ ደረቆት እየተቆረተጠመ በዱር በገደል በውርጭ እቁር እና በፀሀይ ሐሩር እየታገሉ ሀገር ያስከበሩ የቀደምት ሀያቶቻችንን የነደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ፣ የእነ አፄ ሚኒሊክ ፣ የእነ ብርጋዴል ጀናራል አሳምነው ፅጌ ፣ የእነ አፄ ቴድሮስ የትግል አድባር ነው!! ፍኖነት ኢትዮጵያን ከውጭ ወራር እና የውስጥ ባንዳ እተከላከለ ያቆ የብረት አጥር ነው ፡፡ እንሆ እኛም የአባቶቻችን ልጆች ነን እና ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም የትግራይ ወራር ሀይል በሀገር መከላከያ ሀይል በፈፀመው ክደት ክትት መክት ለነፃነት ብለን እኛ አማራ ፋኖዎችም በሬአችን ላማችን ሽጠን የገዛነውን የጦር መሳሪያ ይዘን መከላከያን ከአፈና አድነናል ሀገራችንን ከግዙፍ ውርደት ታድገናል!! ወራርው ትህነግም በዚህ አልቆመም በድጋሚ ወረራ በመጣበት በክረምት ወራት በአባቶቻችን የታሪክ ዉርስ መሠረትጨክትት መክት ብለን ወደ ጦር ግንባር ዘምተናል ፡፡ ክተት መክት ገጀራሀል ይዘ ወጣ ማርከህ ታጠቅም ተብለናል፡፡ ደራሾቹ እኛ ፋኖዎች ከተን ወጥተናል፡፡ ከሀገር መከላከያ እና ከአማራ ልዩ ሀይል ጋር እኩል ተሰልፈን ታግለናል፡፡ ቆሰለናል ሙተናል ደምተናል ማርከን ታጥቀናል ፡፡ ነገር ግን <<እህል ለሰጠ አፈር ወርቅ ለሰጠ ጠጠር >> እንዲሉ አባው እኛ ፋኖዎች ሀገርን ከውርደት በጠበቅን ለሀገራችን እና ለክልላችን የፀጥታ መዋቅር ተጨማሪ አቅም ለሆን ተስድበናል፣ታሥረናል፣ተገለናል፣በም/ቤት .በፓርላማ፣በሚዲያ ፍኖ የታጠቀው መከላኪያ ገሎ ነው ተብለናል፡፡ እኛም ለከጅ ከጅ ይሰጠው ብለን ከክብራችን ሳንወርድ ከክፍታችን ሳንሸራተት እየታገል እንገኛለን፡፡ ገዡ መንግስትም የአማራ ፋኖ ይዘልፋል ጠላታችን ትህነግ/ህውሀትም ፋኖን ይፈርጃል በጋራ እያጠቁን ነው፡፡ የተነሳነለት የአማራ ህዝብም በዚህ ጦርነት ከየትኛውም ክልል በበለጠ መቷል፣ ወድሟል ተጎሳቁሏ፡፡በሚያሳዝን ሁኔታ በድርድሩ ግን ህዝባችን አማራም እንደህዝብ አልተሳተፈም፡፡ ፋኖም ከፍተኛ ዋጋ ብከፍልም በድርድሩ አልተሳተፈም ፡፡ የአማራ ህዝብ ይወክሉኛል ያላቸው 1ኛ ብ/ጄ ተፈራ ማሞ 2ኛ ዶ/ር ደሳለኛ ጫኔ 3ኛ ዶ/ር ወንደሰን አሰፋ 4ኛ አቶ ቴድሮስ ትርፌ እውነተኛ የአማራ ተወካይ እና ተቆርቋሪ በመሆናቸው እንደህዝብ ቅቡልነት ማግኖታቸውን እናውቃለን፡፡ እኛም እንቀበላለን፡፡ እኛ የአማራ ፋኖዎች ሞተናል ፣ቆሰለናል በድርድሩ ወይም በሀገራዊ ምክክሩ የአማራ ፋኖ አንድነት ሊወከል ይገባል፡፡ ከዚህ ውጭ በሆነ መንገድ ግን ከአሸባሪ ህውሃት ጋር እየተደራደረ ያለ መንግስት የፋኖ ትጥቅ እናስፈታለን ብሎ ማለት እና የአማራን ፋኖ ከአሸማሪዎች ጋር በአቻነት እያቀረቡ ፖለቲካ መስራት እየሱስ ክርስቶስን እና በርባንን እንደማወዳደር ይቆጠራል፡፡ ዛሬ የአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤት አመራሮቻችን በመረጥንበትና በአፀደቅነበት በዚሁ ዕለት የሚቀጥለውን ባለ 10 ነትብ የአቋም መግለጫ አውጥተናል ፡፡ 1፣. ወለወቃይት ጠገዴ ጠለምት እና ሪያ የመላው አማራ ህዝብ የፓለቲካ ማጠንጠኛ አስኳላ ሲሆን ከዚህ በፊት የሄዱት በጉልበት እንጅ በህጉ መንግስታዊ ውሳኔ በመሆኑ ፈፅም የማንደራደርባቸው የአማራ ቀይ መስመር ናቸው ፡፡ አጣፈንታችን በክንዳችን እንወስናዋለን፡፡ 2.መንግስት በኩል የአማራን ህዝብ እውነተኛ ጠባቂ የሆነው ፋኖ ትጥቁን ለማስፈታት እና ለመበተን የሚሞክር ሀይል የአማራን ህዝብ እጅህን አስሬ ለጠላት እንሰጥህ ከሚል በሚመነች መሆኑን እንደ ፎኖ እንረደለን፡፡ በመሆኑም ይህ ሊተገበር ይቅር እና መታሰብ የሌለበት ቀይ መስመር መሆኑን እንገልፃለን ፡፡ 3. በሀገራችን የተለያዩ ክልሎች የሚኖሩ የአማራ ተወላጆችን በማንነታቸው ማፈነቀል መግደል እና የዘር ጭፍጨፋ መፈፀም ከጀምረ 32 ዓመት ቢሆንም በተለይም ባላፎት 4 ዓመታት እየተፈፀመ ያለው እንደ ሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ ያለ እና ህግ ባይ መንግስት የሌለው እንዳውም በአንድ የመንግስት አመራሮች መዋቅራዊ ድጋፍ እየተሰጠው መሆኑን እናምናለን፡፡ በተለይም በወለጋ፣ቤኒሻንጉል ጉምዝ እና በደራ አማራን የማፈናቀል እና የማሳደድ መዋቅራዊ ጭፍጨፋውን መንግስት እንደያስቅሞ እንጠይቃለን፡፡ 4. የአማራን ጭፍጨፋ በስሙ በመጥራታቸው ስበባ አስባብ በመፍጠር የታሰሩ ፓለቲከኞች ፣ጋዜጠኞች እና ፎኖዎች ዘመነ ካሴ በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንጠይቃለን፡፡ 5.በሀገራዊ ድርድሩ እና ምክክሩ የአማራ ሁነኛ ተደራዳሪዎቻችን 1ኛ ብ/ጄ ተፈራ ማሞ 2ኛ ዶ/ር ደሳለኛ ጫኔ 3ኛ ዶ/ር ወንደሰን አሰፋ 4ኛ አቶ ቴድሮስ ትርፌ ህዝባዊ ቅቡልነት እንዳላቸው ይታወቃል ፡፡ 6 የአማራ ፋኖ በዚች ሀገር ለከፈለው መስዋትነት ዕውቅና ሊሰጠው እንደሚገባ እናምናለን መንግስታችን ግን በውሃ ቀጠን ስበብ ለመወንጀል የሚያደርገውን ፕሮፓጋንዳ እንዲያቆም እንጠይቃለን ፡፡ 7ኛ በዛሬው ዕለት በተመሰራተው የአማራ ፋኖ አንድነት ም/ቤትነም ብሎ የሚጠይቅ ካለ ተቀራርበን ለመስራት ፣ለአማራ ትግል አጋዥ ነኝ ከሚል ጋርምለ መተባበር ዥግጅ መሆናኝን እንገልፃለን፡፡ 8. የአማራን ክልል ለመበተን እኛ ለማፈራረሥ የሚሰራ ህዝባችን ከግዙፍ ማንነት ወደ ደሀማን ለመቀየር የሚሰራ የፓሊቲካ ስራ ፈፅሞ እንደማንታገስ እንገልፃለን፡፡ 9.የተወላጋዳ አማረኛ የሚናገር አማራ የለም የተወላገደ ህገ መንግስት እንጫንብህ፣እኛ እንውቅልህ በሚል አማራ -ጠል ትርክት በመፍጠር የአማራን ህዝብ ለመክፍፈል የሚሰራ መንግስታዊ አሻጥር በጥብቅ እንቃወማለን፡፡ 10ኛ የተከበርኸው የአማራ ህዝብ ሆይ ዛሬ የመስርትነው አማራ ፋኖ አንድነት ም/ቤት ዋና አለማው የአማራን ህዝብ ሁለንታነዊ መከራ፣ስቆቃ ፣እንግልት ስደት እና ሞት ለመቀለበሥ ብርቱ ህብረት መዳኛ እንደሚሆን በመተማመን የአማራን ህዝብ ለማዳን ቤቴ፣ሚስቴ፣ልጄ ጎጀየ ሳንል ድር ቤቴ ፣ድንጋ ትራሴ ብለን መዳኛህን ተቋም በአንድ እዝ መስርተናል፡፡ ለዚህም በድጋሚ እንኳን ደስአላችሁ እያልን ለመንግስት በኩል የሚፈፀመውን መከባ እና ማሳደድ ከፍኖው እንዲዚህ ቀደሙ ምሽጋችን ፣ጫካችን ትጥቃችን መሳሪያችን ስለሆናቸሁ ፋኖውን ከተኩላዎች እንድት ጠብቁ በአማራ ፋኖ አንድነት ስም ጥሪያችን እናስተላልፋለን ፡፡ ፋኖነት በጀግንነት የሚኖርበት የክብር ስገነት የበረት መስሶ የአማራነት እራስ ነው፡፡ የአማራ ፋኖ አንድነት ቀን ህዳር 13/2015 ዓ.ም ጎንደር ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply