ሰበር መረጃ Update ❗️ የሩሲያ አየር ወለዶች ከዩክሬን ዋና ከተማ ኪዬቭ በ20 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ ደረሱ። ከረፋድ ጀምሮ የሩሲያ አየር ወለዶቹ የዩክሬንን አንቶኖቭ ጦር ካምፕን በቁ…

ሰበር መረጃ Update ❗️ የሩሲያ አየር ወለዶች ከዩክሬን ዋና ከተማ ኪዬቭ በ20 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ ደረሱ። ከረፋድ ጀምሮ የሩሲያ አየር ወለዶቹ የዩክሬንን አንቶኖቭ ጦር ካምፕን በቁጥጥራቸው ስር አስገብተዋል። ባህርዳር :- የካቲት 17/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ በምድር፣ በአየርና በባሕር ሐሙስ ጠዋት በዩክሬን ላይ ጥቃት የከፈተችው ሩሲያ ከፍተኛ ውግዘት እየገጠማት ቢሆንም ዘመቻዋን ቀጥላለች። የሩሲያ ጦር በተለያዩ አቅጣጫዎች ጥቃት የከፈተ ሲሆን ብረት ለበስ ሜካናይዝድ ጦር ፈጣን ግስጋሴ እያደረገ ነው። በዚህም ከደቡብ አቅጣጫ በቤላሩስ ድንበር በኩል እንዲሁም በሰሜን ከክሬሚያ አቅጣጫ ወደ ዩክሬን አምርቷል። በዩክሬን ዋና ከተማ ኪዬቭ የሚገኘው የቢቢሲ ዘጋቢ ፖል አደምስ ሩሲያ በቀጣይ ምን ልታደርግ እንደምትችል ግልጽ አይደለም ብሏል። ምናልባት የአየር ኃይሉን ጦር ካምፕ የተቆጣጠሩት አየር ወለዶች ባሉበት ሆነው ሜካናይዝድ ጦሩን ሊጠብቁ እንደሚችሉ አመልክቷል። አልያም አየር ወለዶቹ የያዙትን የአየር ኃይል ካምፕ በኪዬቭ ላይ የአየር ጥቃት ለመክፈት ይጠቀሙበት ይሆናል ብሏል። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 ዩትዩብ:- https://bit.ly/33XmKro ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 ዩትዩብ:- https://bit.ly/33XmKro

Source: Link to the Post

Leave a Reply