ሰበር ዜና! ሁሉንም የአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች ወደ አንድ ለማምጣት ባህር ዳር ላይ ተሰብስበው እየመከሩ የነበሩ የፋኖ አመራር እና አባላት መንግስታዊ አፈና እንደተፈጸመባቸው እና ወደየት እንደ…

ሰበር ዜና! ሁሉንም የአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች ወደ አንድ ለማምጣት ባህር ዳር ላይ ተሰብስበው እየመከሩ የነበሩ የፋኖ አመራር እና አባላት መንግስታዊ አፈና እንደተፈጸመባቸው እና ወደየት እንደተወሰዱም ለማወቅ አለመቻሉ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ሰኔ 21 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ፋኖ አመራር እና አባላት ባህርዳር ላይ ተሰብስበው የፋኖ አደረጃጀቶችን ወደ አንድ ለማምጣት እየመከሩ እንደነበር የአሚማ ምንጮች ተናግረዋል። አጀንዳቸውም ሁሉንም የአማራ ፋኖ አደረጃጀቶችን ወደ አንድ ለማምጣት ያለመ መሆኑ ተገልጧል። ይሁን እንጅ በስብባው ላይ የነበሩ የአማራ ፋኖ አመራሮችና አባላት ሰኔ 21/2014 ከቀኑ 6 ሰዓት አካባቢ መንግስታዊ አፈና ተፈጽሞባቸዋል፤ ወደየት እንደተወሰዱም ለማወቅ አልቻልንም ሲሉ ምንጮች ተናግረዋል። ከሁሉም የአማራ ግዛቶች የተጠሩ የፋኖ አመራሮችና አባላት እንደሚገኙበት የገለጹት የአሚማ ምንጮች መጀመሪያ ላይ ወደ አፍነው ወደ ልዩ ኃይል ካምፕ ከወሰዱ በኋላ እንደገና አስወጥተው ወዳልታወቀ ስፍራ እንደወሰዷቸው ጠቁመዋል። የታፈኑ የአማራ ፋኖ አመራሮችና አባላትም:_ 1.ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ፣ የአማራ ፋኖ ውህደት አመቻች ኮሚቴ፣ 2.ፋኖ ኢንጅነር በየነ አለማው፣ የአማራ ፋኖ በጎንደር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ፣ 3.ሻለቃ ዳንኤል አስረስ፣ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር፣ የቢትወደድ አዳነ ብርጌድ ዋና አዛዥ፣ 4.ሻለቃ ስጦታው ( የጎቤ መልኬ ታናሽ ወንድም)፣ የጎቤ ብርጌድ አዛዥ፣ 5.ገበየሁ ሞላ የአማራ ፋኖ በጎንደር ሎጅስቲክ ክፍል ኃላፊ፣ 6.ዶ/ር ታደሰ፣ የአማራ ፋኖ በሸዋ አደረጃጀት ኃለፊ፣ 7.አበበ ሙላቱ፣ የአማራ ፋኖ በሸዋ ደ/ብርሃን የምኒልክ ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ፣ 8.ኢሳያስ ደመቀ፣ የአማራ ፋኖ በሸዋ ሎጅስቲክ ክፍል ኃላፊ፣ 9.ታደሠ ፍቅረ፣ የአማራ ፋኖ በሸዋ ሰብሳቢ፣ 10.ሽታየ የትዋለ፣ የአማራ ፋኖ በጎጃም የፍኖተ ሠላም ምክትል ሰብሳቢ፣ 11.ጌታሁን በሬ፣ የአማራ ፋኖ በጎጃም የቡሬ ሻለቃ አዛዥ፣ 12.አትንኩት ሠርፀ ድንግል፣ የአማራ ፋኖ ዉህደት አመቻች ኮሚቴ፣ 13.ሰዋሰው አራጋው፣ የአማራ ፋኖ ውህደት አመቻች፣ 14.ናትናኤል አበባው፣ አመቻች ኮሚቴ አባል መሆናቸውን ለአሚማ የደረሰው መረጃ አመልክቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply