ሰበር ዜና! ላለፉት 25 ቀናት በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና ተባባሪዎቹ እገታ ስር ሆነው 4 ሚሊዮን ብር እንዲከፍሉ የተጠየቁት ሾፌር እና ረዳት ተለቀቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ……

ሰበር ዜና! ላለፉት 25 ቀናት በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና ተባባሪዎቹ እገታ ስር ሆነው 4 ሚሊዮን ብር እንዲከፍሉ የተጠየቁት ሾፌር እና ረዳት ተለቀቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ህዳር 3 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በአዋሽ አርባ ወታደራዊ ት/ቤት የወታደራዊ ተሽከርካሪ ትምህርት እና ስልጠና ክፍል ኃላፊ በመሆን ከ30 ዓመታት በላይ ካገለገሉ በኋላ በጦረታ የወጡት ሌተናል ኮሎኔል አደራ ታዬ እና ረዳታቸው አቶ አስማማው እናውጋው ከ25 ቀናት እገታ በኋላ ህዳር 2/2015 መለቀቃቸውን አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) አረጋግጧል። ከጥቅምት 8/2015 ከቀኑ 11 ሰዓት ጀምሮ በአሸባሪው እና ጸረ አማራው ኦነግ ሸኔ ታግተው 4 ሚሊዮን ብር ክፈሉ ተብለው ቤተሰቦቻቸው የሌላቸውን ገንዘብ በማፈላለግ ለከፍተኛ ጭንቀት ተዳርገው መሰንበታቸው ይታወቃል። ነዋሪነታቸው ደብረ ማርቆስ እና ባሶ ሊበን ኮርክ የሆኑት ታጋቾቹ አይሱዙ ይዘው ከጎጃም ደብረ ማርቆስ ወደ አዲስ አበባ እየተጓዙ እያለ ነው በገብረ በገብረ ጉራቻ እና በጓህ ጽዮን መካከል ቱሉሚልኪ በተባለ በተደጋጋሚ ንጹሃን አማራዎች በሚታገቱበትና በሚገደሉበት አካባቢ ሲደርሱ በሽብር ቡድኑ ታግተው ተወስደው ሰንብተዋል። ከአስከፊው እገታ የሚያስለቅቃቸው የመንግስት አካል ያጡት እነዚህ ሾፌር እና ረዳትም በየጫካው እየተንከራተቱ ብዙ ግፍ ካዩ በኋላ 535 ሽህ ብር ተከፍሎ ተለቀዋል፤ ቤተሰቦቻቸውንም ለመቀላቀል በቅተዋል። ከ3 ዓመት በፊት ጦረታ የወጡት ሌተናል ኮሎኔል አደራው ታዬ እና አስማማው እናውጋው መኪናቸው ተለቆ 4 ሚሊዮን ብር እንዲከፍሉ ተጠይቀው ነበር። በተመሳሳይ ሌላ ጥቅምት 5/2015 ቱሉሚልኪ ላይ የታገቱ ሾፌር እና ረዳት 2 ሚሊዮን ብር ክፈሉ በሚል በእገታ ስር እንደሚገኙም ታውቋል። በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች በአማራ ላይ ከሚፈጸመው የጅምላ ፍጅት በተጨማሪ በየጊዜው በአሽከርካሪዎችና በንጹሃን ተጓዦች ላይ መታወቂያ እየታዬ የሚፈጸመው አሰቃቂ ጥቃት አሳሳቢ ደረጃ ደርሷል፤ የሚያስቆመውም አካል አልተገኘም ሲሉ የሚያማርሩት አያሌ ናቸው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply