You are currently viewing ሰበር ዜና መላው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ጥቁር ልብስ  ብቻ እንዲለብሱ ታወጀ! ጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ ሰሞኑን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላ…

ሰበር ዜና መላው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ጥቁር ልብስ ብቻ እንዲለብሱ ታወጀ! ጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ ሰሞኑን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላ…

ሰበር ዜና መላው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ጥቁር ልብስ ብቻ እንዲለብሱ ታወጀ! ጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ ሰሞኑን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ በተፈጸመው ኢ መደበኛ መፈንቅለ ሲኖዶስ እና መንግስት በድርጊቱ እያሳየ ያለውን ቸለልተኝነት በማስመልከት የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች የመጣባቸውን መከራ ጥቁር ልብስ በመልበስ የነነዌን ጾም በጸሎት እንዲያሳልፉ ቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ ሰቷል:: “የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ ለጾም አዋጅ ነገሩ! ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ።” ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ 3 ቁጥር 5 እንደሚለው ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በተከሰተው ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊና አስተዳደራዊ መዋቅሮቿን በመጣስ መፈንቅለ ሲኖዶስ በማድረግ በሕገወጥ መንገድ ኤጲስ ቆጶስነት ሢመት በሰጡትና በተሾመ ግለሰቦች ላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥር 18 ቀን 2015ዓ.ም. ቃለ ውግዘት ማስተላለፉን አስታውሷል። ይሁን እንጂ እነዚህ ሕገወጥ ቡድኖች ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ካለመቻላቸውም በላይ በመንግሥት ኃይሎች በመታገዝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምታስተዳድራቸውን መንበረ ጵጵስናዎችንና ቢሮዎችን በኃይል በመውረርና በመስበር ከፍተኛ ጥፋት እያደረጉ ከመሆኑም በላይ የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆችን ሠራተኞች ካህናትና ምእመናን በማሰርና በማንገላታት ላይ ይገኛል ብሏል ቅዱስ ሲኖዶስ፡፡ መንግሥትም ሕግ ከማስከበር ይልቅ ለሕገ ወጥ ቡድኖች ድጋፍ በመስጠት የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕግና መብት ሊያስከብር ስላልቻለ ሁሉን ማድረግ ወደሚቻለው አምላካችን በመማፀን ጸሎትና ምሕላ ማድረጉ አስፈላጊ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ተረድቷል በማለት በመግለጫው ተጠቁሟል። በመሆነም ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም የሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን ጥቁር ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት በመገኘት ወደ እግዚአብሔር ጾም፤ ጸሎትና ምሕላ እንድታቀርቡ በማለት ቅዱስ ሲኖዶሱ ጥሪ አስተላልፏል፡፡ ጥቁር ልብስ የምንለብሰው በመከራ መጽናት ለመግለጽ ነው ያለው ቅዱስ ሲኖዶሱ እንደሚታወቀው ጥቁር የእውቀት ምልክት ነው ተማሪዎች አውቀናል ሲሉ ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ ብሏል፡፡ እኛ ከእውቀት በላይ የሆነውን አምላካችንን በመማፀን ከዚህም ማንም ሊያናውጽን እንደማይችል የምናረጋግጥበት፤ ጥቁር የእውነት ምልከት ነው ዳኞች እውነት እንፈርዳለን ሲሉ ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ ያለው ቅዱስ ሲኖዶሱ እኛም መከራው የሚያሰቅቀን ሳይሆን ይበልጥ ልንጸናና ልንበረታ የሚገባ መሆኑን ለዓለም ሕዝብ የምናሳይበት በመሆኑ ከጥር 29 እስከ የካቲት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ለሦስት ቀናት በጾምና በጸሎት በአንድ ልብ ሆነን ወደ ፈጣሪያችንን እንድንጮህ አደራ እንላለን ሲል ቅዱስ ሲኖዶሱ መልዕክቱን አስተላልፏል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply