ሰበር ዜና መንግሥት የተመረጡ የህወሓት ወታደራዊ ዐቅሞች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ! ነሐሴ 20/2014 ዓ.ም (አሻራ ሚዲያ) መንግሥት እስከ አሁን ድረስ ለሰላም በሩን ክፍት አ…

ሰበር ዜና መንግሥት የተመረጡ የህወሓት ወታደራዊ ዐቅሞች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ! ነሐሴ 20/2014 ዓ.ም (አሻራ ሚዲያ) መንግሥት እስከ አሁን ድረስ ለሰላም በሩን ክፍት አድርጎ ቢጠባበቅም ወራሪው የትግራይ ኃይል ጥቃቱን ቀጥሎበታል። በመኾኑም የፌዴራል መንግሥት ያለ ቅድመ ሁኔታ ለመነጋገር የገለጸው… ዝግጁነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ለጁንታው ፀረ ሰላም ዕብሪት ምንጭ የሆኑ ወታደራዊ ዐቅሞችን ዒላማ ያደረገ ርምጃ ይወስዳል ብሏል። ስለኾነም በትግራይ የምትኖሩ ወገኖቻችን በተለይም የጁንታው ወታደራዊ መሣሪያዎች እና ማሠልጠኛዎች ካሉባቸው አካባቢዎች ራሳችሁን እንድታርቁ ይመከራል ሲል የመንግስት ኮምኒኬሽን አስታወቀ :: ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply