ሰበር ዜና! መንግስት መሩ የኦሮሚያ ኃይል በኪረሞ ሀሮ አዲስ ዓለም ላይ በሁለት አቅጣጫ ተኩስ ከፍቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ጥር 3 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ…

ሰበር ዜና! መንግስት መሩ የኦሮሚያ ኃይል በኪረሞ ሀሮ አዲስ ዓለም ላይ በሁለት አቅጣጫ ተኩስ ከፍቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ጥር 3 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ወረዳ ላይ ለአራት ቀናት ጦርነት በመክፈት በርካታ አማራዎችን የገደለው፣ ያቆሰለው እና በሽህ የሚቆጠሩ አማራዎችን ከመኖሪያ ቀያቸው ያፈናቀለው የኦሮሚያ መንግስት መሩ ኃይል በሀሮ አዲስ ዓለም ላይ ህዳር 21 እና ታህሳስ 14/2015 በፈጸመው ከ32 በላይ አማራዎችን መግደሉ ይታወቃል። የገና እና የጥምቀት በዓልን ተከትሎም ከነቀምት እና ከጊዳ አያና ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ወደ ኪረሞ ማስገባቱን ተከትሎ የወረራ ጦርነት ሊከፍት ይችላል በማለት ነዋሪዎች የድረሱልን ጥሪ አሰምተው ነበር። መንግስት መሩ የኦሮሚያ ኃይል በቡድን መሳሪያ ጭምር በመታገዝ ጥር 3/2015 ሀሮ አዲስ ዓለም ላይ በ2 አቅጣጫዎች ማለት በኪረሞ እና በሰምቦ በኩል ተኩስ መክፈቱን ለማወቅ ተችሏል። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) በቀጥታ ደውሎ ያነጋገራቸው የሀሮ አዲስ ዓለም ነዋሪዎች እንዳሉት መንግስት መሩ ኃይል ጦርነት መክፈቱን ተከትሎ ለመረጃ ልውውጥ ስለሚያስፈልገው በጸረ አማራ ጥላቻ ይታወቃል በተባለው በኪረሞ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ በሆነው በእነ አቶ ፍቃዱ ሁንዴ ተዘግቶ የከረመውን ኔትወርክ ክፍት አድርጓል ብለዋል። መከላከያ ሰራዊት ከሀሮ አዲስ ዓለም በቅርብ ርቀት ጊዳ አያና እና አንገር ጉትን ላይ መኖሩ ቢታወቅም ትዕዛዝ እየተሰጠው ባለመሆኑ ህዝቡን ለመታደግ አልቻለም።

Source: Link to the Post

Leave a Reply