ሰበር ዜና! ሱዳን የስልጠና ድጋፍ የሚሰጣቸው አሸባሪዎች በመተማ ወረዳ ቱመት መንዶካ ቀበሌ በሌሊት በፈጸሙት ጥቃት የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ፤ 4 ቆስለዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ……

ሰበር ዜና! ሱዳን የስልጠና ድጋፍ የሚሰጣቸው አሸባሪዎች በመተማ ወረዳ ቱመት መንዶካ ቀበሌ በሌሊት በፈጸሙት ጥቃት የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ፤ 4 ቆስለዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ሀምሌ 3 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ሱዳን የስልጠና ድጋፍ የሚሰጣቸው አሸባሪዎች በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ቱመት መንዶካ ቀበሌ በሌሊት በፈጸሙት ጥቃት የ5 ሰዎች ህይወት ማለፉ እና 4 መቁሰላቸው ተነግሯል። የቡድን መሳሪያ እና ገጀራ በመጠቀም ሀምሌ 2/2014 ከሌሊቱ 6 ሰዓት ተኩል ጀምሮ በፈጸሙት የወረራ ጥቃት ተገድለዋል። የሕወሓቱ ሳምሪ አሸባሪ ቡድን አባላትና የሕወሓት ቅጥረኛ እና ጽንፈኛ የቅማንት ኮሚቴ አባላት እንዲሁም የጉምዝ የታጠቀ የሽፍታ ቡድን በጥምረት በፈጸሙት ጥቃት ነው ጉዳቱ የደረሰው። ከተገደሉት መካከልም አንዷ ሴት መሆኗ ተገልጧል። ቆስለው ከነበሩት 5 ሰዎች መካከል አንዱ ገንዳውሃ እንደደረሰ ህይወቱ አልፏል። የቆሰሉትም በሙሉ ከሽንፋ ጤና ጣቢያ ወደ ገንዳውሃ ሆስፒታል ነው የተላኩት። ከ30 በላይ የመኖሪያ ቤቶችንም አቃጥለዋል። በቀላል ግምት ከ2 ሽህ በላይ የቀንድ ከብት፣ ፍየሎች፣በጎችና የጋማ ከብቶችን ዘርፈዋል፤ በርካቶችንም ጭምር በጥይትና በእሳት አቃጥለዋል። ጭፍጨፋውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ያለማንም ተከላካይ ፈጸመው ወጥተዋል። እነዚህ አሸባሪዎች ማሰልጠኛ ካምፓቸው ቲሃ እና ማርያም ተራራ በተባለ አካባቢ ነው። ሀምሌ 2/2014 የቡድን መሳሪያ እየተኮሱ ውለዋል። ሱዳን በትጥቅ፣ በስንቅ እና በመረጃ የምትደግፋቸው እነዚህ ሽብር ቡድን አካላት በመርትራድ አካባቢ ከአንድ ሳምንት በፊት በአንድ ባለሃብት የእርሻ ካምፕ ገብተው ዘበኛውን በመግደል ትራክተሩን አቃጥለዋል። ኢንዲቪሎ በተባለ አካባቢም የባለሃብት አቶ ሀብታሙ እና አቶ አለማየሁ የተባሉ ተወካይ የሚሰሩበት የእርሻ ካምፖችንም በማቃጠል ዘርፈዋል። የሽንፋ ቀበሌ አስተዳዳሪን የአቶ በለጠ ዳምጤን የእርሻ ካምፕ ሰኔ 15/2014 አቃጥለዋል። በተለይም የቱመት መንዶካ ቀበሌ የሚያለሙ ኢንቨስተሮችና አርሶ አደሮችን በተለይ መርትራድ፣ ኢንዲቪሎ በሚባሉ አካባቢዎች ከ300 በላይ አፈናቅለዋል። ጭፍጨፋ እና ዝርፊያ የፈጸሙ አካላትም ድርጊቱን ከፈጸሙ በኋላ ቲሃ ወደሚባል አካባቢ ተሻግረው ገብተዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply