
#ሰበር ዜና! ሸዋ ደራ በፌዴራል ፖሊስ ስም ገብቶ የነበረው ሃይል በደራ ማንነት ኮሚቴ አመራሮች ላይ አፈና እና ጥቃት ለማድረስ ሞክረዋል ተባለ! መጋቢት 14 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ ሸዋ ደራ በፌድራል ፖሊስ ስም ገብቶ የነበረው ኃይል የቱቲን ሚኒሻዎችን አብረን እንዝመት ብሎ አብረው ከዘመቱ በኋላ የደራ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊውን አቶ አሰፋ ነበበን ለማፈን ጥረት አድርጎ በሚኒሻው ጥረት ቢከሽፍም ምሽት አካባቢ በሩ ላይ ጠብቀው የግድያ ሙከራ አድረገው አልተሳካላቸውም ሲሉ የአሻራ ምንጮች ገለፁ። ስለሆነም 👉ለሚዲያ አካላት 👉ለሲቪል ተቋማት 👉ለፖለቲካ ፖርቲዎች 👉ለአማራ ፋኖ አንድነት 👉ለአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሸዋ ደራ የአማራ ማህበረሰብ ላይ የሚደርሰውን ግፍ እና በደል እንድታውቁልን እና ለምናደርገው ትግል ከጎናችን እንዲትቆሙ ጥሪ እናስተላልፋለን ሲሉ ተናግረዋል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post