You are currently viewing ሰበር ዜና! በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ያሉ ሊቃነ ጳጳሳት በአስቸኳይ ወደ መንበረ ፓትርያርክ እንዲመጡ ጥሪ ቀረበ።   አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ …     ጥር 14 ቀን 2015 ዓ/ም…

ሰበር ዜና! በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ያሉ ሊቃነ ጳጳሳት በአስቸኳይ ወደ መንበረ ፓትርያርክ እንዲመጡ ጥሪ ቀረበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ጥር 14 ቀን 2015 ዓ/ም…

ሰበር ዜና! በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ያሉ ሊቃነ ጳጳሳት በአስቸኳይ ወደ መንበረ ፓትርያርክ እንዲመጡ ጥሪ ቀረበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ጥር 14 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ! መግለጫውን የሰጡት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፖትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አሥኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ በመንበረ ፓትርያርክ የተገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው። ቅዱስነታቸው ዛሬ ማለዳ በተሰማው ሕገ ወጥ “ሢመተ ጳጳሳት” ጉዳይ በሰጡት መግለጫ ጉዳዩ ከቅዱስ ሲኖዶስ እውቅና ውጪ በሕገ ወጥነት የተከናወነ መሆኑን በመግለጽ :- 1. በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ያሉ ሊቃነ ጳጳሳት በአስቸኳይ ወደ መንበረ ፓትርያርክ እንዲመጡ ጥሪ ቀርቧል። 2. መንግሥት ክስተቱ በሀገር ላይ ጭምር የሚያስከትለውን ጉዳት ተመልክቶ በጉዳዩ ላይ ሕጋዊ ሓላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል። 3. ምዕመናን ቤተክርስቲያንን ከመቸውም ጊዜ በላይ በንቃት እንዲጠብቁ ቅዱስነታቸው ጥሪ አቅርበዋል። መረጃው: EOTCTV

Source: Link to the Post

Leave a Reply