ሰበር ዜና በልደታ ክ/ከተማ ስልጤ መስጅድ ጀርባ በፈነዳ ቦንብ የሰው ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ አሻራ ሚዲያ… ታህሳስ…

ሰበር ዜና በልደታ ክ/ከተማ ስልጤ መስጅድ ጀርባ በፈነዳ ቦንብ የሰው ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ አሻራ ሚዲያ… ታህሳስ፡-11/04/13/ዓ.ም ባህር ዳር ታህሳስ 11 ቀን 2013 ዓ/ም ከጠዋቱ 2፡30 ሠዓት በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ስልጤ መስኪድ ጀርባ ለልማት በፈረሰ ክፍት ቦታ ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች ተጥሎ በተገኘ የእጅ ቦንብ በጎዳና ተዳዳሪ የሆኑ የሦስት ሰዎች ህይወታቸው አልፏዋል፡፡ በአምስት ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የልዩ ልዩና የተደራጁ ወንጀሎች ምርመራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር አለማየሁ አያልቄ ከፍንዳታው ጋር በተያያዘ ያለው የምርመራ ሂደት እየተጣራ መሆኑን ገልፀው የምርመራ ውጤቱ እንደተጠናቀቀ ለህብረተሰቡ ግልጽ ይደረጋል ብለዋል፡፡ ኃላፊው ባስተላለፉት መልዕክት በተለያዩ ቦታዎች እንደ አልባሌ በሚጣሉ ቦንቦችና ፈንጂዎች ንፁሀን ሰለባ መሆናቸውን አስታውሰዋል፡፡ በመጨረሻም ህብረተሰቡ ምንነታቸው ያልታወቁ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት ከመነካካት በመቆጠብ ለሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ጥቆማ ማድረግ እንደሚገባ ሀላፊው አሳስበዋል፡፡ ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply