
ሰበር ዜና! በመርሃቤቴ ወረዳ የአለም ከተማ ሆስፒታል በሙትና ቁስለኛ የአገዛዙ ሰራዊት ተጥለቅልቋል‼ ሐምሌ 15 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ በሰሜን ሸዋ ዞን መርሃቤቴ ወረዳ ከአለም ከተማ በቅርብ ርቀት በሚገኘው ጎምሹ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የህዝብ ልጅ በሆኑት ፋኖዎች እና በብልፅግና ፓርቲ ወታደሮች መካከል ትናንት ሀምሌ 13/2015 ዓ/ም አመሻሹን ከባድ ውጊያ ተካሂዷል። በዚህ ውጊያ የሸዋ አናብስቱ በወሰዱት መብረቃዊ የሆነ አፀፋዊ ምት 30 የሚደርሱ የብልፅግና ፓርቲ ወታደሮች ሲደመሰሱ ከ40 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቆስለዋል ነው የተባለው። በአሁን ሰዓት በአለም ከተማ እናት ተብሎ የሚጠራው ሆስፒታል ክፍኛ በቆሰሉ በብልፅግና ቡድን ወታደሮች ተጨናንቋል ሲሉ ሁኔታውን የተመለከቱ የአይን እማኞች ለአማራ ድምፅ ገልፀዋል። አንድ የፋኖ አባል በታጠቀው ክላሽ የአገዛዙን ዙ 23 መሣሪያ ለማውደም ከጠላት ኃይል ጋር አንገት ላንገት ተናንቆ ስለ አማራ ህዝብ ህልውና ሲል በክብር መውደቁንም ምንጮቻችን ጠቅሰዋል። ዘገባው የአማራ ድምፅ ነው። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- Ashara Tv – https://www.youtube.com/channel/UC2LZu_N0iOJipVUw3RyR4Ng // https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post