ሰበር ዜና በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ በጉምዝ ታጣቂዎች ታግተው የነበሩ 4 ቱ ሲለቀቁ 1ሰው ህይወቱ አለፈ።               አሻራ ሚዲያ      ህዳር 1/2013 ዓ.ም ባህር ዳር……

ሰበር ዜና በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ በጉምዝ ታጣቂዎች ታግተው የነበሩ 4 ቱ ሲለቀቁ 1ሰው ህይወቱ አለፈ። አሻራ ሚዲያ ህዳር 1/2013 ዓ.ም ባህር ዳር……

ሰበር ዜና በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ በጉምዝ ታጣቂዎች ታግተው የነበሩ 4 ቱ ሲለቀቁ 1ሰው ህይወቱ አለፈ። አሻራ ሚዲያ ህዳር 1/2013 ዓ.ም ባህር ዳር… በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ቁጥር 3 ተብሎ የሚጠራው አካባቢ ከ4 ቀን በፊት በጉምዝ ታጣቂዎች ታግተው የነበሩ አራት (4)ሴት እና አንድ(1) በድምሩ 5 አማራዎችን አግቶ የነበረ ሲሆን በዛሬው እለት የመከላከያ ሰራዊት በአጋቾች ላይ እርምጃ በመውሰድ 4 ሴቶችን ያስለቀቀ ሲሆን አንደኛው ወንድ ታጋች ህይወቱ ማለፉን የመረጃ ምንጫችን ከቢታው ገልፆልናል። የመከላከያ ሰራዊት አባላቱ ለ3 ቀን ያክል ከጉምዝ ታጣቂዎች ጋር ውጊያ ሲያደርግ የነበረ ሲሆን በዛሬው እለት በነበረው የተኩስ ልውውጥ ከአጋቾቹ መካከል ሶስት(3) የጉምዝ ታጣቂዎች ሲገደሉ የተቀሩት ታጋቾችን ጥለው አምልጠዋል። ታጋቾቹም በዓሁኑ ሰዓት ከማንቡክ 50 km እርቀት ላይ ቢዝር ቀበሌ በላያ አካባቢ ሲሆኑ ሁሉም ሴቶች በመልካም ጤንነት ላይ እንዳሉ የገለፁልን የመረጃ ምንጫችን በነገው እለትም ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንደሚገናኙም ይጠበቃል ብለዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply