ሰበር ዜና! በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ በዝግህ ቀበሌ በእርሻ ማሳቸው ላይ ያሉ ከ50 ያላነሱ አርሶ አደሮች በጉምዝ ታጣቂዎች መከበባቸውን በመግለፅ የድረሱልን ጥሪ አቀረቡ።…

ሰበር ዜና! በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ በዝግህ ቀበሌ በእርሻ ማሳቸው ላይ ያሉ ከ50 ያላነሱ አርሶ አደሮች በጉምዝ ታጣቂዎች መከበባቸውን በመግለፅ የድረሱልን ጥሪ አቀረቡ።…

ሰበር ዜና! በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ በዝግህ ቀበሌ በእርሻ ማሳቸው ላይ ያሉ ከ50 ያላነሱ አርሶ አደሮች በጉምዝ ታጣቂዎች መከበባቸውን በመግለፅ የድረሱልን ጥሪ አቀረቡ። አሻራ ሚዲያ ታህሳስ 7/2013ዓ•ም ባህርዳር በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ዝግህ በተባለ ቀበሌ በእርሻ ማሳቸው ሆነው የደረሰ ሰብላቸውን በመሰብሰብ ላይ ያሉ 50 አርሶ አደሮች በጉምዝ ታጣቂዎች ከበባ የተደረገባቸው መሆኑን በመግለፅ መንግስት እንዲደርስላቸው ጠይቀዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች በዝግህ ከተማ የሚገኙ የመከላከያ ሰራዊትም ለታፈኑት አርሶ አደሮች ትዕዛዝ አልደረሰንም በማለት ፈጣን ምላሽ አለመስጠታቸው እንዳሳሰባቸው ተናግረዋል። ታጋቾቹም በዋናነት አማራዎች ሱሆኑ በተጨማሪም ኦሮሞ፣ ሽናሻና የሌላ ብሄር ተወላጆች እንዳሉበትም ተገልጧል። የዝግህ ቀበሌ ም/አስተዳዳሪ አቶ ከበደ ከጉምዝ ታጣቂዎች ጋር በመሆን በወንጀል ድርጊቱ አስተኳሽነት እየተሳተፈ ነው ብለዋል ነዋሪዎቹ። ከረፋዱ 3 ሰዓት ጀምሮ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት 7:30 ሰዓት ድረስ ከተከበቡት መካከል ያነጋገርናቸው የዝግህ ቀበሌ ነዋሪ ከከተማዋ 1 ሰዓት ርቀት ላይ 50 የሚደርሱ ሴቶች፣ህጻናት ጭምር ያሉበት አርሶ አደሮች የደረሰ ሰብል በመሰብሰብ ላይ እያሉ በጉምዝ ታጣቂዎች ከበባ ተደርጎ ተኩስ እንደተከፈተባቸው ገልፀዋል። እስካሁን አንድም የፀጥታ አካል አልደረሰልንም ያለው ታጋቹ መንግስት አደጋ ላይ መሆናችን ተረድቶ በአስቸኳይ ደርሶ እንዲታደገን የሚል ጥሪ አቅርቧል። የድባጤ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኩመራ በእኛ በኩል የተረጋገጠ መረጃ የለንም፤ ይሁን እንጅ መረጃውን ለኮማንድ ፖስት ሪፖርት አድርገናል ብለዋል። ከአካባቢው ከአቅማችን በላይ ነው የሚል ሪፖርት አልደረሰንም፤ ግን እንዳረጋገጥን ችግሩን ለመፍታት የምንሰራ ይሆናል ብለዋል። ዘገባው:- የአማራ ሚዲያ ማዕከል ነው

Source: Link to the Post

Leave a Reply