ሰበር ዜና! በመንግስት አካላት ጭምር እንደሚደገፍ የሚነገርለት ጽንፈኛ እና የታጠቀ የኦነጋዊያን ስብስብ በሸዋ አጣዬ፣ በካራቆሬ፣ ቆሪሜዳና በሸዋሮቢት መግቢያ ላይ ጭምር ተኩስ በመክፈት በሰው…

ሰበር ዜና! በመንግስት አካላት ጭምር እንደሚደገፍ የሚነገርለት ጽንፈኛ እና የታጠቀ የኦነጋዊያን ስብስብ በሸዋ አጣዬ፣ በካራቆሬ፣ ቆሪሜዳና በሸዋሮቢት መግቢያ ላይ ጭምር ተኩስ በመክፈት በሰው…

ሰበር ዜና! በመንግስት አካላት ጭምር እንደሚደገፍ የሚነገርለት ጽንፈኛ እና የታጠቀ የኦነጋዊያን ስብስብ በሸዋ አጣዬ፣ በካራቆሬ፣ ቆሪሜዳና በሸዋሮቢት መግቢያ ላይ ጭምር ተኩስ በመክፈት በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ መሆኑን ነዋሪዎች ገለፁ፤ ከጥቃቱ ለማምለጥ በመሸሽ ላይ ያሉ ወገኖችም የድረሱልን ጥሪ አስተላልፈዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ሚያዝያ 8 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በመንግስት አካላት ጭምር እንደሚደገፍ የሚነገርለት ጽንፈኛ እና የታጠቀ የኦነጋዊያን ስብስብ በሸዋ አጣዬ፣ በካራቆሬ፣ ቆሪሜዳና በሸዋሮቢት መግቢያ ላይ ጭምር ተኩስ መክፈቱ ተገልጧል። በጥቃቱም በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ መሆኑን ከአጣዬ፣ከካራቆሬ እና አካባቢው ከጥቃቱ ለመትረፍ ወደ ጫካ እየሸሹ ያሉ ነዋሪዎች ተናግረዋል። ዛሬ ሚያዝያ 8 ቀን 2013 ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ በአጣዬ፣በካራቆሬ፣በቆሪሜዳና አካባቢው የተደራጀ እና በቡድን መሳሪያ የታጀበ ተኩስ በመክፈት ጉዳት እያደረሱ ነው። ከአጣዬ ከተማ እየሸሹ ያሉ ነዋሪ እንደገለፁት እየደረሰ ያለው ጉዳት አሳሳቢ መሆኑን ጠቅሰዋል። ከርቀት በመትረጊዬስ እንዲሁም ወደከተማው በአራት አቅጣጫ እየገቡ በመተኮስ አማራዎችን እየገደሉ ነው፤ የአጣዬ ከተማ አስተዳደሩን ጨምሮ የመንግስትና የግል ተቋማትን እያወደሙ ይገኛሉ ብሏል። የመከላከያ ሰራዊት፣የፌደራል ፖሊስና ልዩ ኃይሉ በጋራ ሆነው እየታገሉ መሆኑን የገለፁት ነዋሪው ነገሩ ከበድ ያለ እየሆነ ነው ብለዋል። የታጠቁት መሳሪያም በአይነቱ ለየት ያለ ነው፤ ህጻናትና አቅመ ደካሞችን ሁሉ የማይምሩ ሰዋዊ አውሬዎች ገጥመውናል ብለዋል። ተጨማሪ ኃይል አስፈላጊ መሆኑን በመጠቆም። ካራቆሬ ያነጋገርናቸውም በተመሳሳይ ወደ ጫካ እየሸሹ መሆናቸውን ጠቁመው በሸዋሮቢት መግቢያ አካባቢም ተኩስ መክፈታቸውን ተናግረዋል። የአጣዬ ከተማ ከንቲባ አቶ ደምስ አበበን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ስልካቸው ባለመስራት ለጊዜው አልተሳካም። ሙሉ ቆይታችንን በአሚማ የዩቱብ አድራሻ ይጠብቁ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply