ሰበር ዜና! በምስራቅ ወለጋ ዞን ሊሙ ወረዳ በአርቁምቢ መንደር 5 እና መንደር 6 ሁለት አብያተ ክርስቲያናትን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ የመኖሪያ ቤቶች መውደማቸው ተገለፀ፤  ታቦት ተሸክመው…

ሰበር ዜና! በምስራቅ ወለጋ ዞን ሊሙ ወረዳ በአርቁምቢ መንደር 5 እና መንደር 6 ሁለት አብያተ ክርስቲያናትን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ የመኖሪያ ቤቶች መውደማቸው ተገለፀ፤ ታቦት ተሸክመው…

ሰበር ዜና! በምስራቅ ወለጋ ዞን ሊሙ ወረዳ በአርቁምቢ መንደር 5 እና መንደር 6 ሁለት አብያተ ክርስቲያናትን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ የመኖሪያ ቤቶች መውደማቸው ተገለፀ፤ ታቦት ተሸክመው ጫካ በርሃብ ላይ ያሉ የሀይማኖት አባትና እናቶችን አነጋግረናል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሚያዝያ 8 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል በምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና እና በሊሙ ወረዳዎች በተለይም በመንደር 8,9,10 እና በአርቁምቢ 01 ቀበሌ መንደር 5 እና 6 ነዋሪ በሆኑ አማራዎች ላይ ግድያ፣ማሳደድና ዝርፊያ ሲፈፅም መሰንበቱን የገለፁት ነዋሪዎች መከላከያ ሰራዊት ይግባልን በሚል ጥሪ ብናቀርብም ሰሚ መንግስት አላገኘንም ብለዋል። የኦሮሚያ ልዩ ኃይልን ተገን በማድረግ ተደራጅተው ጥቃትና ቃጠሎ የሚፈፅሙ ዘራፊዎችም በዛሬው እለት ሚያዝያ 8 ቀን 2013 ከንጋት ጀምሮ በሊሙ አርቁንቢ 01 ቀበሌ በመንደር 5 እና 6 የሚገኙ የመድሃኒያለምንና የአቦ ቤተ ክርስቲያንን አቃጥለዋል ተብሏል። የመድሃኒያለም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የነበሩ 3 ታቦቶችን ይዘው በጫካ የተሰደዱ አባቶች፣ሴቶችና ህጻናት የተማፅኖ ጥሪ አቅርበዋል። እናቶችም እያለቀሱ እራበን፣ በጎን ለመግደል በየጫካው እያሳደዱን ነው፤ ምን ይሻላል? በፈጣሪ ድረሱልን በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል። የኦሮሚያ ክልል መንግስት የልዩ ኃይል አባላትን አትግደሉ፣አትዝረፉ ብሎ የሚያስቆም አካል አልተገኘም ያሉት ተጎጅዎቹ ባንዴራ ይዘው ለማስቆም የገቡ የመከላከያን ሰረሰዊት አባላትን ከገደሉ በኋላ አማራ ገደለ በማለት ስም እያጠፉ ነው ብለዋል። በጫካ ካሉ የሀይማኖት አባቶችና ከእናቶች ጋር ያደረግነውን ቆይታ በአሚማ የዩቱብ አድራሻ ይጠብቁ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply