ሰበር ዜና! በምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤሊያስ ወረዳ በጃቢ ገነት ቀበሌ መንግስታዊ አፋኝ ቡድኑ ተኩስ ከፍቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ግንቦት 13 ቀን 2014 ዓ.ም…

ሰበር ዜና! በምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤሊያስ ወረዳ በጃቢ ገነት ቀበሌ መንግስታዊ አፋኝ ቡድኑ ተኩስ ከፍቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ግንቦት 13 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤሊያስ ወረዳ በጃቢ ገነት ቀበሌ በአንድ ፋኖ ቤት ከበባ በማድረግ መንግስታዊ አፋኝ ቡድኑ ተኩስ ከፍቷል የሚሉት የአሚማ ምንጮች ተጨማሪ ኃይል በፓትሮል ጭነው ወደ አካባቢው እየተጓዘ መሆኑን ገልጸዋል። ግንቦት 13/2014 ከቀኑ 10 ሰዓት ተኩል ጀምሮ በህዝብ ላይ ከባድ ተኩስ ከፍተዋል የሚሉት ምንጮች ደጀን እና ጫጎ በሚባሉ አካባቢዎች በ5 ፓትሮል አሰሳ ሲያደርጉ ከቆዩ በኋላ ተመልሰው ጃቢ ገነት በተባለች የገጠር ከተማ ተኩስ ከፍተዋል ብለዋል። ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት እስከ ምሽት 3 ሰዓት ከ30 ድረስ በተለይም በጃቢ ገነት አርጎት በተባለ ወንዝ አካባቢ ተኩሱ እንደቀጠለ ነው የተገደሉ እና የቆሰሉ ሰዎችን በተመለከተ መረጃው እንደሌላቸው ነው የደብረ ኤሊያስ ነዋሪዎች የገለጹት። በህግ ማስከበር ስም በአማራ ላይ የተከፈተው መንግስታዊ አፈና አሁንም ተጠናክሮ እንደቀጠለ ስለመሆኑ የሚገልጹት ምንጮች በምዕራብ ጎጃም ዞን ሰሜን ሜጫ ወረዳ መራዊ አካባቢ ከፍተኛ የሆነ አፋኝ ጦር እየተከማቸ መሆኑ ለከፍተኛ ስጋት ዳርጎናል ብለዋል። ግንቦት 12/2014 መንግስታዊ አፋኝ ቡድኑ በመርዓዊ፣ በሞጣ እና በወልድያ ከፍተኛ ግድያ፣እስር እና ወከባ መፈጸሙ ይታወሳል። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ተጨማሪ መረጃ እንዳገኘ የሚመለስ ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply