You are currently viewing ሰበር ዜና! በምዕራብ ጎጃም ዞን የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ም/ሰብሳቢ አሸናፊ አካሉ ወዳልታወቀ ስፍራ ታፍኖ ተወሰደ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…   ግንቦት 8 ቀን 2014 ዓ.ም…

ሰበር ዜና! በምዕራብ ጎጃም ዞን የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ም/ሰብሳቢ አሸናፊ አካሉ ወዳልታወቀ ስፍራ ታፍኖ ተወሰደ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ግንቦት 8 ቀን 2014 ዓ.ም…

ሰበር ዜና! በምዕራብ ጎጃም ዞን የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ም/ሰብሳቢ አሸናፊ አካሉ ወዳልታወቀ ስፍራ ታፍኖ ተወሰደ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ግንቦት 8 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ለውጥ ይመጣል በሚል ላለፉት በርካታ ዓመታት ከፍተኛ የነጻነት ትግል ሲያደርግ የቆዬውና ለዓመታት በእስር የተሰቃዬው አሸናፊ አካሉ ወዳልታወቀ ስፍራ ታፍኖ ተወስዷል። አፈናው የተፈጸመው በልዩ ኃይል እና በፖሊስ ሲሆን ሌሊቱን በባህዳር ዳር ቀበሌ 14 አኮቴት አካባቢ የመኖሪያ ቤቱ ተከቦ ማደሩ ተገልጧል። አሚማ ለማጣራት እንደሞከረው ግንቦት 8/2014 ከንጋቱ 11 ሰዓት ላይ የጸጥታ አካላት አፍነው ወስደውታል። አሸናፊ አካሉ በምዕራብ ጎጃም ዞን ቀደም ሲል የአብን ሰብሳቢ በመሆን በቅርቡ ደግሞ በምክትል ሰብሳቢነት እየሰራ እንደነበር ይታወቃል። ባለቤቱ ወ/ሮ ሰላም መላኩም በበኩሏ ቤቱን ከቦ ያደረ ከ20 በላይ የሚሆን ልዩ ኃይል እና ፖሊስ ለጥያቄ እንፈልግሃለን በሚል ንጋት ላይ አፍነው ወስደውታል ብላለች። ከኢህአዴግነት ተቀይሬ ብልጽግና ሆኛለሁ የሚለው ስርዓት ከመጣ ጀምሮ ላለፉት 4 ዓመታት የጅምላ ዘር ተኮር ፍጅት፣የኢኮኖሚ ድቀት፣ እስር እና ወከባው በእጅጉ ተባብሶ ስለመቀጠሉ የሚናገሩት ብዙዎች ሂደቱን ለውጥ ሳይሆን ነውጥ ነው ሲሉ ይደመጣሉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply