You are currently viewing ሰበር ዜና! በሰሜን ሸዋ ዞን ጀውሃን ጨምሮ ወሰን ቁርቁር እንዲሁም ጀጀባ እና ሰንበቴ ላይ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ተኩስ መክፈታቸው ተገለፀ! ጥር 15 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣…

ሰበር ዜና! በሰሜን ሸዋ ዞን ጀውሃን ጨምሮ ወሰን ቁርቁር እንዲሁም ጀጀባ እና ሰንበቴ ላይ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ተኩስ መክፈታቸው ተገለፀ! ጥር 15 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣…

ሰበር ዜና! በሰሜን ሸዋ ዞን ጀውሃን ጨምሮ ወሰን ቁርቁር እንዲሁም ጀጀባ እና ሰንበቴ ላይ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ተኩስ መክፈታቸው ተገለፀ! ጥር 15 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ ስር በሚገኘው ጀውሃ ቀበሌን ጨምሮ ወሰን ቁርቁር፣ ጀጀባ እና ሰንበቴ ላይ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ዛሬ ጥር 15/2015 ዓ/ም ከረፋዱ ጀምሮ ተኩስ መክፈታቸውን የአከባቢው ነዋሪዎች ለአማራ ድምፅ ገልፀዋል። በአማራ ክልል የኦሮሞ ልዩ ዞን ስር መሽገው የሚገኙት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ጥር 13/2015 ዓ/ም አመሻሹን በኤፍራታና ግድም ወረዳ ጀውሃ ቀበሌ በሚገኘው የአማራ ልዩ ኃይል ካምፕ ላይ ጥቃት ከፍተው የነበረ ሲሆን፣ በዚህም ከ30 በላይ ልዩ ኃይሎች መገደላቸው ታውቋል። ታጣቂዎቹ በድጋሚ ዛሬ ጥር 15/2015 ዓ/ም ከረፋዱ ሦስት ሰዓት ገደማ ጀምሮ በኤፍራታና ግድም ወረዳ ስር በምትገኘው ጀውሃ ቀበሌን ጭምሮ ወሰን ቁርቁር፣ ጀጀባ እና ሰንበቴ ላይ በቡድን መሳሪያ ጭምር የታገዘ ተኩስ መክፈታቸውን ነው የአከባቢው ነዋሪዎች ለአማራ ድምፅ ያረጋገጡት። በአከባቢው የሚገኙት የክልሉ ልዩ ኃይሎች በታጣቂዎቹ የተከፈተውን ጥቃት ለመከላከል ሙከራ እያደረጉ ነው የተባለ ሲሆን ነገር ግን ተኩሱ አድማሱን እያሰፋ መሆኑ ተመላክቷል። የአማራ ድምፅ ሚድያ ያነጋገራቸው የጀውሃ ቀበሌ ነዋሪዎች፡ “አከባቢውን ለቀን እንዳንወጣ መንገድ ተዘግቷል” ያሉ ሲሆን የክልሉ መንግስት ተጨማሪ የፀጥታ ኃይል አሰማርቶ እንዲታደጋቸው ጥሪ አቅርበዋል። በኦሮሚያ ልዩ ዞን የጅሌ ሙጥጋ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ቢሮ በበኩሉ “ሰንበቴ ከተማ ጭንቅ ውስጥ ገብታለች” ሲል በማህበራዊ ትስስር ገፁ ያሰፈረ ሲሆን የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎቹ የአማራ ተወላጅ የሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች ላይ እርምጃ እየወሰዱ መሆኑን ነው የአማራ ድምፅ ካሰባሰበው መረጃ ማረጋገጥ ችለናል ሲል የአማራ ድምፅ ዘግቧል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply