
ሰበር ዜና በሰሜን ወሎ ዞን ጋዞ ወረዳ 4 የፖሊስ አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው የምስራቅ አማራ ፋኖን መቀላቀላቸው ተሰማ‼ ሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ በዚህ የተደናገጠው የሰሜን ወሎ ዞን ጋዞ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት የሌሎች ፖሊስ አባላትን ትጥቅ በማስፈታት ወደ የቤታቸው እየበተነ መሆኑ ታውቋል። “በድንገት ለስራ ትፈለጋላችሁ በሚል በተናጥል ወደ ፖሊስ ፅ/ቤቱ እየጠሩ ነው ትጥቃችንን ያስወረዱን፣ለምን ብለን ስንጠይቅ፣ሰራዊቱ ከነ ሙሉ ትጥቁ እየከዳን ስለሆነ እናንተም እንዳትከዱ ስለሰጋን ነው”የሚል መልስ እንደሰጧቸው በስልክ መረጃ ያቀበሉን አካላት ገልፀዋል። የጋዞ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት ኃላፊ የሆነው ኮማንደር አስማረ እና የወረዳው ኮሚኒቲንግ ፖሊስ ኃላፊው ዋና ሳጅን ደጀኔ በዋናነት ትጥቅ የማስፈታቱን ስራ እየከወኑ እንደሆነ ታውቋል። በሰሜን ወሎ ዞን ጋዞ ወረዳ የሚገኙ የ32ኛ ዙር ፖሊስ አባላት መሳሪያቸው ከተገፈፈ በኋላ ከቀጣይ ወር ጀምሮ ደሞዝ እንደማይከፈላቸው በመግለፅ ሀሉም አባላት ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲበተኑ ተነግሯቸዋል።በሌሎች የአማራ ከተሞች የሚገኙ የ32ኛ ዙር ፖሊስ አባለት መሳሪያቸው ተገፎ ሊበተኑ መሆኑን ከወዲሁ በመረዳት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ፋኖን እንዲቀላቀሉ መረጃ የሰጡን አካላት ጥሪ አቅርበዋል። በአዊ ዞን ዳንግላ ወረዳ ጥሩ ብርሃን ማሰልጠኛ ኮሌጅ መጋቢት 9/2015 ዓ.ም ከ6400 በላይ ምልምል የፖሊስ አባላት ለ32ኛ ዙር ስልጥነው መውጣታቸው ይታወቃል። እነዚህ የፖሊስ አባላት በወር 1968 ብር ደሞዝ እንደሚከፈላቸው ታውቋል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- Ashara Tv – https://www.youtube.com/channel/UC2LZu_N0iOJipVUw3RyR4Ng // https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post