ሰበር ዜና በባህር ዳር ከተማ ከጁንታዉ ህዉሓት ጋር ገንኙነት አለዉ የተባለዉ ወጣት እዮብ ታምሩ ታሰረ         አሻራ ሚዲያ    ህዳር 5/2013 ዓ.ም ባህርዳር ህዉሓት…

ሰበር ዜና በባህር ዳር ከተማ ከጁንታዉ ህዉሓት ጋር ገንኙነት አለዉ የተባለዉ ወጣት እዮብ ታምሩ ታሰረ አሻራ ሚዲያ ህዳር 5/2013 ዓ.ም ባህርዳር ህዉሓት…

ሰበር ዜና በባህር ዳር ከተማ ከጁንታዉ ህዉሓት ጋር ገንኙነት አለዉ የተባለዉ ወጣት እዮብ ታምሩ ታሰረ አሻራ ሚዲያ ህዳር 5/2013 ዓ.ም ባህርዳር ህዉሓት በሰሜን ዕዝ ላይ የክህደት ጭፍጨፋ ካደረገ ጀምሮ በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የህዉሓትን ተልዕኮ ተቀብለዉ ለእኩይ ተግባር ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦች እና ቡድኖችን ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን በቁጥጥር ስር እያዋለ እንደሆነ ስማቸዉ እንዳይገለፅ ያልፈለጉ የመረጃ ምንጫችን ለአሻራ ሚዲያ ገልፀዋል፡፡ በዛሬዉ እለትም በባህር ዳረ ከተማ ነዋሪ የሆነዉ ወጣት እዮብ ታምሩ ከጁንታዉ ህዉሓት ጋር ግንኙነት በመፍጠር ለህዉሓት መረጃ ሲያቀብል ነበር በሚል ተጠርጥሮ መታሰሩን የመረጃ ምንጫችን ገልፀዉልናል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ወጣት እዮብ ታምሩ በትናንትናዉእለት የህዉሓት የእሮኬት ጥቃትን በቀጥታ በተንቀሳቃሽ ምስል/ቪዲዮ/ የጠላት ፕሮፓጋንዳ ማሰራጫ ለሆነዉ <>እና ለሌሎች የጠላት ሚዲያዎች መረጃ በማቀበል ህዝብን በማሸበር ላይ እንደነበርም የመረጃ ምንጫችን ገልፀዉልናል፡፡ በመጨረሻም በሁሉም የክልላችን አካባቢዎች እንዲህ አይነት አኩይ አላማ ይዘዉ የሚንቀሳቀሱ ሀይሎች ሊኖሩ ስለሚችሉ ህብረተሰቡ አካባቢዉን ነቅቶ እንዲጠብቅ እና የተለየ አንቅስቃሴ ሲያዩ ለአካባቢዉ የፀጥታ ይል እንዲጠቁም ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply