ሰበር ዜና በንፁሀን ደም በምትታጠበው መተከል ዛሬም ንጹሀን ዜጎች እየተጨፈጨፉ መሆኑ ተገለጸ፡፡                 አሻራ ሚዲያ…

ሰበር ዜና በንፁሀን ደም በምትታጠበው መተከል ዛሬም ንጹሀን ዜጎች እየተጨፈጨፉ መሆኑ ተገለጸ፡፡ አሻራ ሚዲያ…

ሰበር ዜና በንፁሀን ደም በምትታጠበው መተከል ዛሬም ንጹሀን ዜጎች እየተጨፈጨፉ መሆኑ ተገለጸ፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳር፡-15/03/13/ዓ.ም ባህር ዳር በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ አይጋሊና ዶቢ በርካታ ንፁሃን በግፍ እየተጨፈጨፉ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። አስከሬን በየጫካው ወድቆ እየተገኘ ነው። ለማምለጥ ሲሉ በየጫካው የገቡት በህይወት ስለመኖራቸው ማረጋገጥ በማይቻልበት ሁኔታ በርካቶች ጠፍተዋልም ብለዋል። የሚደርስባቸውን ጥቃት ሸሽተው የተሰደዱት ደግሞ በየአካባቢው በከፍተኛ ሠብአዊ ቀውስ ውስጥ እንደሚገኙም የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ በመጨረሻም መንግስት በአስቸኳይ ይድረስልን ሲሉ ከጭፍጨፋው ያመለጡ ነዋሪዎች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ዘጋቢ፡- ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply