
ሰበር ዜና! በአባይ ሸለቆ ብርጌድ መሪ በፋኖ ሙሉቀን አደራው እና በጓዶቻቸው ላይ የግድያ ሙከራ ተደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ሀምሌ 15/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ሐምሌ 12/ 2015 ዓ.ም አባይ ሸለቆ መሸጎ በሚገኘው የአባይ ሸለቆ ብርጌድ መሪ ሙሉቀን አደራው ላይ እና አብረዋቸው በነበሩት የኃይል ሦስት አባላት ላይ ከሌሊቱ 11፡40 አካባቢ ቦንብ (F1) በመወርወር መሪውን እና አመራሮችን በመግደል ጀግናውን የአባይ ሸለቆ ብርጌድ ለመበተን ሙከራ መደረጉ ታውቋል። መረጃውን ከቦታው ያደረሡን ፋኖ አሻግሬ ባየ እንደገለፁት የታቀደው የግድያ ሙከራ ባይሳካም በሁለት የብርጌዱ አባላት ላይ መካከለኝ ጉዳት ደርሷል ብለዋል። የቦንብ ጥቃት ያደረገውን አካል በሁለት ቀናት በተደረገ ጥብቅ ክትትል በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን በደጃዝማች ወራየ ሰኞ ገበያ በሞትባል ከተማ በህዝብ አደባባይ አውጥተው ለህዝብ በይፋ አሳይተዋል። ጥቃቱን የፈፀመው ከብልፅግና ተልዕኮ የወሰደ አንድ ሰርጎ ገብ ባንዳ እንደሆነ ፋኖ አሻግሬ ባየ ተናግሯል። አሁን ላይ የብርጌዱ መሪ ፋኖ ሙሉቁን አደራው ብርጌዱን በብስለት እየመሩ ሲሆን ህዝቡ ላደረገለን እና ለሚያደርግልን ድጋፍ ላቅ ያለ ምስጋና አለን ብለዋል። አክለውም መግደል ስራችን ስላልሆነ እንጅ እንዲህ አይነቱን ባንዳ ማስወገድ ተገቢ ነበር ነገር ግን በአማራዊ ስብዕና አስተምረን ልከነዋል ብለዋል። አሻራ ሚዲያ እንደዘገበው።
Source: Link to the Post