ሰበር ዜና! በአዲስ አበባ የሚኖሩ የወለጋ አማራ ተወላጆች ኢሰመጉ በወለጋ አማራዎች ላይ እየተፈጸመ ስላለው ግድያ፣እገታ፣መፈናቀል እና መሳደድ ጉዳይ በትኩረት እንዲሰራ መረጃ ለመስጠትና ለማሳ…

ሰበር ዜና! በአዲስ አበባ የሚኖሩ የወለጋ አማራ ተወላጆች ኢሰመጉ በወለጋ አማራዎች ላይ እየተፈጸመ ስላለው ግድያ፣እገታ፣መፈናቀል እና መሳደድ ጉዳይ በትኩረት እንዲሰራ መረጃ ለመስጠትና ለማሳሰብ ባቀኑበት በፖሊሶች ታፈኑ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ህዳር 24 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በአዲስ የሚኖሩ የወለጋ አማራ ተወላጆች በወለጋ አማራዎች ስርዓታዊ መልክ እየያዘ የመጣው የጅምላ ግድያ፣ እገታ፣ዝርፊያ እና መፈናቀልን በተመለከተ ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) መረጃ ለመስጠትና ትኩረት እንዲሰጡት ለማሳሰብ ህዳር 24/2015 ከቀኑ 9:30 ላይ አቅንተው እንደነበር ተገልጧል። ቁጥራቸውም ከ30 እስከ 40 የሚደርሱ ሲሆኑ ቀደም ሲል በተሰጣቸው ቀጠሮ መሰረት በልደታ ክ/ከተማ ከኢሰመጉ ቢሮ ገብተው ከተወያዩ እና መረጃ ሰጥተው ከቢሮ ሲወጡ ሲከታተሏቸው በቆዩ ፖሊስ ሌላ ቢሮም መረጃ ትሰጣላችሁ በሚል ወስደው እንዳሰሯቸው ተሰምቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ያነጋገራቸው የመረጃ የምንጮች እንደሚሉት መጀመሪያ ላይ ከዛጉዌ ህንጻ ፊት ለፊት ባለው ልደታ ፖሊስ ጣቢያ ከታሰሩ በኋላ አመሻሹን ወደ ጎማ ቁጠባ ፖሊስ ጣቢያ የቀየሯቸው መሆኑን ገልጸዋል። ከታሰሩት ወጣቶች መካከልም:_ 1) ሙላቱ ወዳጅነው፣ 2) ሰይድ ሀሰን፣ 3) ሰይድ ሁሴን፣ 4) የሱፍ ኢብራሂም፣ 5) አስቻለው፣ 6) ዮናስ ይመር፣ 7) ቢራራ እባቡ እና 8 አብርሃም ደሳለኝ የተባሉ በአዲስ አበባ የሚኖሩ የወለጋ አማራዎች ይገኙበታል። የአማራ ተወላጆች በተለይም ከሰሞኑ በኪረሞ፣በሀሮ አዲስ ዓለም፣ በሰቀላ፣በጃርዴጋ፣ በጊዳ አያና አንዶዴ ዲቾ እና አንገር ጉትን የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ከአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና ከሌሎች የአካባቢው የጸጥታ አካላት ግድያ፣እገታ፣ዝርፊያ እና መፈናቀል እየገጠማቸው ስለመሆኑ እየገለጹ ነው። አሚማ ተጨማሪ መረጃ እንዳገኘ የሚያጋራ ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply