You are currently viewing ሰበር ዜና! በእስር ላይ የሚገኙት 46 የባልደራስ አመራር፣አባላት፣ ደጋፊዎች እና የአዲስ አበባ ወጣቶች ከተማ ዳር ወደሚገኘው አባ ሳሙኤል እስር ቤት ተወሰዱ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ……

ሰበር ዜና! በእስር ላይ የሚገኙት 46 የባልደራስ አመራር፣አባላት፣ ደጋፊዎች እና የአዲስ አበባ ወጣቶች ከተማ ዳር ወደሚገኘው አባ ሳሙኤል እስር ቤት ተወሰዱ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ……

ሰበር ዜና! በእስር ላይ የሚገኙት 46 የባልደራስ አመራር፣አባላት፣ ደጋፊዎች እና የአዲስ አበባ ወጣቶች ከተማ ዳር ወደሚገኘው አባ ሳሙኤል እስር ቤት ተወሰዱ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… መጋቢት 1 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምርመራ ላይ ያሉ እስረኞች ወደ አባ ሳሙኤል ሲወሰዱ ይህ የመጀመሪያው ነው። በአድዋ እና ካራማራ ሳቢያ የተከሰሱት 34 የባልደራስ እስረኞችን ጨምሮ 46 የአዲስ አበባ ወጣቶች ዛሬ በምሳ ሰዓት ታስረው ከሚገኙበት አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከተማ ዳር ወደሚገኘው አባ ሳሙኤል ተዛዋውረዋል፡፡ ይህ ፍፁም ያልተጠበቀ እና ህገ ወጥ እርምጃ ሲሆን፣ እስካሁን ባለው አሰራር ተጠርጣሪዎች መደበኛ የክስ ፋይል እስካልተከፈተባቸው ድረስ ወደ አባ ሳሙኤል አይሄዱም፡፡ ተጠርጣሪዎች የምርመራ ጊዜያቸውን የሚያሳልፉት ጊዮርጊስ በሚገኘው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እስር ቤት ወይም በየወረዳው ባሉ የፖሊስ ጣቢያ እስር ቤቶች ነው፡፡ እርምጃው መንግሥት በህገወጥ እና በጉልበት አካሄዱ እየገፋበት እንደሆነ ያመላክታል፡፡ የባልደራስ አባላት እና ሌሎች የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ተጠርጥረው በተያዙበት ጉዳይ ዛሬ ማለዳ አራዳ ጊዮርጊስ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በ3 የጊዜ ቀጠሮ መዝገብ ቀርበዋል፡፡ ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው የጊዜ ቀጠሮ ጥያቄ፣ “ተጠርጣሪዎቹ በአድዋና በካራማራ ክብረ-በዓላት ላይ ሁከትና ብጥብጥ በማነሳሳት፣ ህዝብ በመንግሥት ላይ እንዲያምጽ በማድረግ፣ የመንግሥት ባለስልጣናትን በመሳደብና በማዋረድ ተግባር ላይ ሲሰማሩ አግኝቻቸዋለሁ፤ እንዲሁም፣ የተከለከለ ሰንደቅ ዓላማ በመያዝ በመንግሥት ላይ አመጽ ለማነሳሳት ሞክረዋል” ብሏል፡፡ ስለሆነም “በተጠርጣሪዎቹ ላይ ምርመራ እንድናደርግባቸው የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ” ብሏል፡፡ የተከሳሾቹ ጠበቆች ባቀረቡት ክርክር፣ “ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለማየት የሥረ-ነገር ሥልጣን የለውም፤ ጉዳዩም መታየት ካለበት የወንጀል ተግባሩ ተፈፀመ በተባለበት በልደታ ክፈለ ከተማ አጥቢያ ፍርድ ቤት ነው፣ በአንድ የወንጀል ጉዳይ ሁለት የጊዜ ቀጠሮ መዝገብ ልደታ እና አራዳ ክፍለ ከተማ ሊከፈት አይገባም፣ ፖሊስ 48 ሰዓት ካለፈ በኋላ ያቀረበው የጊዜ ቀጠሮ ጥያቄ ውቅድ ሊሆን ይገባል” ብለዋል፡፡ በተጨማሪም “ተጠርጣሪዎቹ ከ5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የተዛወሩት እስረኞችን ለመበቀል፣ ሆን ብሎ ለማንገላታትና በረዥም ጊዜ ቀጠሮ ያለአግባብ ለማጉላላት ነው” ሲሉ ወቅሰዋል፡፡ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እያሉ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቀርበው የ3 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ከተሰጣቸው በኋላ፣ ፖሊስ በእለቱ ለይግባኝ ሰሚ ችሎት የይግባኝ አቤቱታ ቢያቀርብም፣ ችሎቱ የፖሊስን አቤቱታ ውድቅ ማድረጉን ጠቅሰዋል። “በ3 ቀን ውስጥ አጣርቶ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ በተሰጠበት ሁኔታ፣ በተሰጠው ጊዜ ውስጥ የምርመራ ስራውን ሰርቶ ማቅረብ ሲገባው፣ ይህንን ወደ ጎን በመተው ለፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት አዲስ የጊዜ ቀጠሮ መዝገብ ማስከፈቱ ተጠርጣሪዎቹን ለመበቀል አላማ እንደሆነ መረዳት ይቻላል” ብለዋል፡፡ በተጨማሪም፣ ፖሊስ በቀን የካቲት 23 የአድዋ በዓል እና የካራማራ የድል በዓል ላይ ሁከትና ብጥብጥ ተፈፀመ ቢልም፣ በእለቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሰጠው መግለጫ በዓሉ በሰላም ተጠናቋል የሚል መግለጫ አውጥቶ እያለ፣ መስተዳድሩ የማያውቀው ሁከትና ብጥብጥ እንደተፈፀመ ተደርጎ በፖሊስ የቀረበው ክርክር ውድቅ እንዲደረግ ተጠይቋል፡፡ እንዲሁም፣ ፖሊስ ባቀረበው አቤቱታ የድል በዓላቱ በሚከበርበት ጊዜ የባለሥልጣናት ስም ተነስቶ የስድብ እና ማዋረድ እንደተፈፀመ ቢያቀርብም፣ ጉዳዩ በግል አቤቱታ አቅራቢነት የሚቀርብ ሆኖ ሳለ፣ ባለሥልጣናቱ ቀርበው ምርመራ እንዲጣራላቸው አቤቱታ ወይም ማመልከቻ ለፖሊስ ባላቀረቡበት ሁኔታ፣ ፖሊሰ በራሱ ተነሳሽነት ሊያጣራው የሚችለው ባለመሆኑና ጊዜ ቀጠሮ የሚያስጠይቅ ባለመሆኑ የፖሊስ አቤቱታ ውድቅ እንዲደረግ ተጠይቋል፡፡ በተያያዘም፣ የተከለከለ ሰንደቅ አላማ ይዘው ወጥተዋል በሚል ያቀረበውን በተመለከተም፣ በአዋጅ ቁጥር 654/2001 መሠረት ጥፋተኛ ሆነው ቢገኙ እንኳን፣ በገንዘብ አማራጭ የሚያስቀጣ ቀላል ጉዳይ በመሆኑ፣ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ፖሊስ ያቀረበው አቤቱታ ከወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዓት ህጉ አላማና ግብ ያፈነገጠ በመሆኑ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ሊሰጥ አይገባም ሲሉ ጠበቆቹ ተከራክረዋል፡፡ ፖሊስ አሰባስባችኋል ያላቸው የሰነድ፣ የሰው እና የስልክ ማስረጃዎች ቀጠሮ ለማሰጠት በቂ አይደሉም፡፡ የማያውቋቸው ምስክሮች እና አባሪዎች ሊያሸሹብኝ ይችላሉ ያለውን ስማቸው ተጠቅሶ ያላወቅናቸው ስለሆነ ተገቢነት ያለው አይደለም ብለው ጠበቆች ተከራክረዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም በጠበቆች ክርክር ላይ ፖሊስ መልስ እንዲሰጥ ካደረገ በኋላ ትዕዛዝ ለመስጠት ለመጋቢት 5/2014 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ በእለቱ በርካታ ቁጥር ያለው የአዲስ አበባ ነዋሪ በችሎቱ አዳራሽ እና ከአዳራሽ ውጭ ተገኝቶ ጉዳዩን ተከታትሏል፡፡ ለዘገባው የባልደራስ ሚዲያ ክፍልን በምንጭነት ተጠቅመናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply