ሰበር ዜና! በደቡብ ኢትዮጵያ ሰገን አካባቢ ህዝቦች ዞን በጉማይዴ ወረዳ ጋርጠራ በተባለ አካባቢ ታጣቂዎች በጦር መሳሪያ በመታገዝ የነዋሪዎችን መንደር እያቃጠሉ መሆኑ ተነገረ። አማራ ሚዲያ ማ…

ሰበር ዜና! በደቡብ ኢትዮጵያ ሰገን አካባቢ ህዝቦች ዞን በጉማይዴ ወረዳ ጋርጠራ በተባለ አካባቢ ታጣቂዎች በጦር መሳሪያ በመታገዝ የነዋሪዎችን መንደር እያቃጠሉ መሆኑ ተነገረ። አማራ ሚዲያ ማ…

ሰበር ዜና! በደቡብ ኢትዮጵያ ሰገን አካባቢ ህዝቦች ዞን በጉማይዴ ወረዳ ጋርጠራ በተባለ አካባቢ ታጣቂዎች በጦር መሳሪያ በመታገዝ የነዋሪዎችን መንደር እያቃጠሉ መሆኑ ተነገረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ጥር 1 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በደቡብ ኢትዮጵያ ሰገን አካባቢ ህዝቦች ዞን በጉማይዴ ወረዳ ልዩ ስሙ ጋርጠራ በተባለ ቀበሌ ታጣቂዎች ዛሬ ጥር 1 ቀን 2013 ዓ.ም ከማለዳው 3 ሰዓት ጀምሮ በጦር መሳሪያ በመታገዝ የገጠር መንደሮችን በሙሉ እያቃጠሉ መሆኑን ነው ነዋሪዎች የገለፁት። አካባቢውን እያወደሙ ያሉት ታጣቂዎች የደቡብ ክልል የልዩ ሀይል ልብስን የለበሱ መሆናቸውን የገለፁት የጉማይዴ ወረዳ ነዋሪዎች ከጥቅምቱ 2013ቱ ውድመት የተረፈውን መንደር አሁን እየጨረሱ ይገኛሉ በማለት ነው አስከፊነቱን የገለፁት። በሽብር ተግባር የተሰማሩት የጥፋት ኃይሎች የገጠሩን መንደር ክፉኛ እያወደሙ ወደ ሰገን ከተማ ቀያጤ ያለማንም ከልካይ እየገሰገሱ ይገኛሉ፤ ሌሊቱን ሊገቡ ስለሚችሉ እባካችሁ መንግስት ካለ ይድረስልን ሲሉ ተማፅነዋል። በአካባቢው ያሉ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ አመራሮችም ከአካባቢው ነዋሪዎች ከፍተኛ የድረሱልን ጭሆት እየደረሳቸው መሆኑንና በመንግስት ድጋፍ ያላቸው ኃይሎች ከፀጥታ አካላት ጋር ተባብረው በጉማይዴ ጥፋት እያደረሱ ነው ብለዋል። የበርካታ ብሄረሰብ ተወላጆች ያሉበት ጉማይዴ ከተቃጠለ ነገም የእኛ ተራ ነው ሲሉ ነው አንድ የደራሼ ነዋሪ ስጋታቸውን ያጋሩት። በመንግስት የልዩ ኃይል አባላት ይታገዛሉ የተባሉት የተደራጁ የጥፋት ኃይሎች በጥቅምት ወር 2013 ዓ.ም ከ67 በላይ ነዋሪዎችን የገደሉ ሲሆን በሽህ የሚቆጠሩ ወገኖችን በኮንሶ፣በአማሮ፣ በደራሼ እና በአሌ አካባቢ ማፈናቀላቸው ይታወሳል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply