You are currently viewing ሰበር ዜና! በደቡብ ወሎ ዞን ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲያቀኑ የነበሩ የሀርቡ ፋኖዎች የአፈና እስር ተፈጸመባቸው፤ በሁለት ቀን ብቻ 5 አባላቱ ታፍነዋል፤ ምን አደረጉ ይለቀቁልን ብለው በጠየቁ አ…

ሰበር ዜና! በደቡብ ወሎ ዞን ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲያቀኑ የነበሩ የሀርቡ ፋኖዎች የአፈና እስር ተፈጸመባቸው፤ በሁለት ቀን ብቻ 5 አባላቱ ታፍነዋል፤ ምን አደረጉ ይለቀቁልን ብለው በጠየቁ አ…

ሰበር ዜና! በደቡብ ወሎ ዞን ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲያቀኑ የነበሩ የሀርቡ ፋኖዎች የአፈና እስር ተፈጸመባቸው፤ በሁለት ቀን ብቻ 5 አባላቱ ታፍነዋል፤ ምን አደረጉ ይለቀቁልን ብለው በጠየቁ አባላትና አመራሮች ላይ ተኩስ መከፈቱን ተከትሎ ወደ ጫካ ለመሸሽ ተገደዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ግንቦት 21 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የደቡብ ወሎ ፋኖ በአማራ የተለያዩ አካባቢዎች በህግ ማስከበር ስም ካለፉት ሶስት ሳምንታት ጀምሮ በቀጠለው አፈና፣እስር እና ወከባ በርካታ አመራሮችና አባላቱ እየታሰሩና እየተሳደዱበት እንደሚገኝ ይታወቃል። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ለማጣራት እንደሞከረውም ግንቦት 20/2014 ዓ/ም 3 የሀርቡ ፋኖ አባላት መንግስት ባሰማራው ግብረ ኃይል ታፍነው ተወስደዋል። ግጠሙ እና ፋኖን በትኑ የተባሉት የአካባቢው ሚሊሾች ለዚህ ግዳጅ በሚልም ለማበረታቻ በሚል ለእያንዳንዱ የሚሊሻ አባል ግንቦት 21 ከረፋዱ ላይ በሀርቡ እነ አስር አለቃ ስንታየሁ ጌታቸው በደቡብ ወሎ ዞን የሀርቡ ፋኖ ዘመቻ መምሪያ የሚመሩት፣ እነ ኤርሚያስ አያሌው በሚመሩት በደቡብ ወሎ ፋኖ ስር ያለውን ይህን የፋኖ አደረጃጀት ትጥቅ በማስፈታት ለመበተን በሚል ታቅዶ እየተሰራ ነው ተብሏል። ለፋኖ ድጋፍ ታደርጋለህ በሚል አቶ አህመድ የሱፍ የተባለ የሀርቡ ነዋሪ ግንቦት 20/2014 ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ታፍኖ ተወስዷል፤ በሀርቡ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ ይገኛሉ። 1) ፋኖ መሀመድ የሱፍ፣ 2) ፋኖ ይብሬ ካሱ እና ሌላ አንድ ለጊዜው ስሙ ያልታወቀ የሀርቡ ፋኖ አባል ግንቦት 20/2014 ታፍነው ተወስደዋል። 3) ፋኖ አወቀ ጤናው እና 4) ፋኖ አብርሃም አብነው የተባሉ የሀርቡ ፋኖ አባላትም በተመሳሳይ ግንቦት 21/2014 ከንጋቱ 12/2014 ወደ ቤተ ክርስቲያን እየሄዱ ባሉበት ድንገት ከበባ ተደርጎ ታፍነዋል። የሀርቡ ፋኖዎችም ንጹሃን አመራሮችና አባላቶቻችን “ስለምን ይታፈናሉ? ይፈቱልን?” ብለው ሽማግሌ ከመላክ አልፈው በአካል ሄደው ለማነጋገር ሲሞክሩ “ምን አገባችሁ?” በሚል ግንቦት 21/2014 ከረፋዱ 4:30 ላይ ለአጭር ጊዜ ተኩስ እንደተከፈተባቸው አስታውቀዋል። ከጥቃት ራሳችን ለመከላከል ስንልም የአጸፋ ምላሽ በመስጠት አሁን ላይ በርካቶች ወደ ጫካ ለመግባት ተገደናል ብለዋል። የሀርቡ ወረዳ ፖሊስ እና አድማ በታኞች ይህን የአፋና ተግባር እንዲፈጽሙ ትዕዛዝ የተሰጣቸው መሆኑ ተገልጧል። የአካባቢው ሚሊሾች በትግሉ አብረውን ከተሰው፣ከደሙና ከቆሰሉ ፋኖ ወንድም እና እህቶቻችን ጋር አንገዳደልም በመሆኑም ለዚህ ተግባር አንተባበርም በማለት ከስምሪቱ ስለመበተናቸው ተገልጧል። የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ የደረሳቸው መረጃ አለመኖሩን የተናገሩት የአሚማ ምንጮች ከኮምቦልቻ ተጨማሪ አፋኝ ኃይል እየተላከ መሆኑን ሰምተናል ብለዋል። በዋናነት ለፋኖ ካላቸው ጥላቻ፣ ካደገባቸው የመላላክ ባህርይና ብልሹ ስራ አኳያ ሲሉ የገለጿቸው የሚከተሉት የወረዳ እና የቀበሌ አመራሮች ፋኖን ትጥቅ ለማስፈታትና ለማሰር እየተንቀሳቀሱ ነው:_ 1) ኮማንደር ይመር_የሀርቡ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ_በዋናነት ኃይል እየላከ ፋኖን የሚያሳፍን ነው ተብሏል። 2) ኮማንደር ጀማል_የወረዳው የፖሊስ አዛዥ፣ 3) አቶ ያሲን አህመድ_የተባሉ የከተማ ከንቲባ ስለመሆናቸው ተገልጧል። ከደቡብ ወሎ ፋኖ ከሰሞኑ ብቻ በዘመቻው ከታፈኑት መካከል:_ 1.ፋኖ ሙሉጌታ የሺጥላ የደቡብ ወሎ ፋኖ ሰብሳቢ፣ 2.ፋኖ ዘላለም ጫኔ የደቡብ ወሎ ፋኖ ም/ሰብሳቢ፣ 3.ፋኖ አማረ ወርቄ የደቡብ ወሎ ፋኖ ፋይናንስ ሀላፊ፣ 4.ፋኖ አረጋ ታደሰ አባል፣ 5.ፋኖ ይመር ሰይድ፣ 6.ፋኖ ሰይድ መሀመድና ሌሎችም ይገኙበታል። ስለጉዳዩ የተጠየቁት የሀርቡ ከተማ ከንቲባ አቶ ያሲን አህመድ በበኩላቸው “ውሸት ነው” ብለው ካስተባበሉ በኋላ በፋኖነታቸው እና በደጋፊነታቸው የታሰሩ ከተባሉት መካከል የተወሰኑ አባላትን በስም ከተጠቀሱላቸው ውጭ 35 የአካባቢው ነዋሪዎች ተጠርጥረው ስለመታሰራቸውም ገልጸዋል። በደቡብ ወሎ ደሴ በአማራ ፋኖዎች ላይ ትጥቅ የማስፈታት እና ለማስፈታት የተጀመረው አፈና ለጊዜው በገራዶ እና ጢጣ (ኬላ) ቢከሽፍም ከበባው ግንቦት 21/2014 ቀጥሎ ስለመዋሉ ታውቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply