ሰበር ዜና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሚመራው የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት ዋናውን የወልድያ መቀሌ ጎዳና ቆርጦታል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሚመሩት የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት፣ በአ…

ሰበር ዜና
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሚመራው የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት ዋናውን የወልድያ መቀሌ ጎዳና ቆርጦታል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሚመሩት የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት፣ በአሸባሪው ወራሪ ላይ በሰነዘሩት ክንደ ብርቱ ማጥቃት፣ በምሥራቅ ግንባር ስትራቴጂያዊ የሆኑትንና ወራሪው በፍጻሜ ዋዜማ ላይ መሆኑን የሚያሳዩትን የዞብል ሠንሠለታማ ተራሮችን ጨምሮ ከፍተኛ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያላቸውን የአርጆ፣ ፎኪሳ እና ቦረን ከተሞችን ተቆጣጥሯል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ የጉራ ወርቄ አካባቢዎችን በመቆጣጠር የወልድያ መቀሌ ዋናውን አውራ ጎዳና በመቁረጥ ጠላት መውጫ አጥቶ ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚሁ ግንባር የድሬ ሮቃና የሶዶማ ከፍተኛ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ከተሞችና ተራሮች በመቆጣጠር ጥምር ጦሩ ወደ ሐራ ከተማ እየገሠገሠ ይገኛል፡፡

በውጫሌ ግንባር ደግሞ የአምባሰል ከፍተኛ ሠንሠለታማ ተራሮችን ጨምሮ የሮቢትና የጎልቦን፣ በወረባቦ ወረዳ የሚሌ ኮትቻን፣ በሐብሩ ወረዳ የኮልቦን፣ የመርካታና የፋጂን አካባቢዎችን በመቆጣጣር ወደ መርሳ ከተማ እየገሠገሠ ነው፡፡
በእነዚህ ግንባሮች በተደረገው ኦፐሬሽን በአሸባሪው የጠላት ኃይል ላይ በተሠነዘረበት ማጥቃት ጠላት ሙት፣ ቁስለኛና ምርኮኛ ሆኗል፡፡
የወገን የመካናይዝድ ኃይልና ንሥሮቹ የአየር ኃይሉ በጥምረት ባካሄዱት ኦፐሬሽን የጠላት ኃይል ምንም ዓይነት ተሸከርካሪ እና ከባድ መሣሪያዎችን ይዞ እንዳይንቀሳቀስ ስላደረጉት፣ ጠላት በየአቅጣጫው ጥሎ ለመፈርጥጥ ተገድዷል፡፡

ነጻነታችንን የምናረጋግጠው በተባበረ ክንዳችን ነው!
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
ታህሳስ 02 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply