You are currently viewing ሰበር ዜና! በ20 ሽህ ብር ዋስትና በክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤቱ እንዲለቀቁ የመፍቻ ትዕዛዝ የተጻፈላቸው የአማራ ፋኖ በባህር ዳር አባላት ተለይተው እንዲፈቱ ስማቸው ተጠርቷል፤ ይሁን እንጅ በ25…

ሰበር ዜና! በ20 ሽህ ብር ዋስትና በክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤቱ እንዲለቀቁ የመፍቻ ትዕዛዝ የተጻፈላቸው የአማራ ፋኖ በባህር ዳር አባላት ተለይተው እንዲፈቱ ስማቸው ተጠርቷል፤ ይሁን እንጅ በ25…

ሰበር ዜና! በ20 ሽህ ብር ዋስትና በክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤቱ እንዲለቀቁ የመፍቻ ትዕዛዝ የተጻፈላቸው የአማራ ፋኖ በባህር ዳር አባላት ተለይተው እንዲፈቱ ስማቸው ተጠርቷል፤ ይሁን እንጅ በ25 ሽህ ብር ዋስትና እንዲፈቱ የተወሰነላቸው 14ቱ የአማራ ፋኖዎችንም ካልተፈቱ አንወጣም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ሀምሌ 25 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ያነጋገራቸው ባህር ዳር ወጣቶች እንደገለጹት በግፍ የታሰሩና በዋስትና እንዲወጡ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት የተወሰነላቸው ሁሉም ፋኖዎች እንዲወጡ በሰባታሚት ማረሚያ ቤት በር አካባቢ ዛሬም ከጠዋት ጀምሮ ተሰብስበው ውለዋል። በ20 ሽህ ብር ዋስትና በክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤቱ እንዲለቀቁ የመፍቻ ትዕዛዝ የተጻፈላቸው የአማራ ፋኖ በባህር ዳር አባላት ተለይተው ሃምሌ 25/2014 ከቀኑ 7: 30 አካባቢ እንዲፈቱ ስማቸው በማ/ቤቱ ተጠርቷል። ይሁን እንጅ 6ቱ የአማራ ፋኖ በባህር ዳር አመራሮችና አባላት ይህ የተለመደ ነጣጥሎ የማጥቃት አካሄድ ነው በሚል ውድቅ አድርገውታል። ጉዳያችን ተመሳሳይ ነው እኛ ተለይተን የምንፈታበት ምክንያት ግልፅ አይደለም በመሆኑም ማ/ቤቱ ህግን የሚያከብር ከሆነ በ25 ሽህ ብር ዋስትና እንዲፈቱ የተወሰነላቸውን 14ቱ የአማራ ፋኖዎችን ጭምር አብሮ ሊፈታ ይገባል ሲሉ አካሄዱን አውግዘዋል። እነሱ ካልተፈቱ እኛም አካሄዱ ሁሉ ከህግ ውጭ መሆኑን ስለምንገነዘብ ተለይተን አንወጣም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ምንጮች ለአሚማ እንደሚሉት የሰባታሚት ማረሚያ ቤትም አንወጣም ካላችሁ መፍቻውን እንመልሰዋለን በማለት እያንገራገረ ነው። የባህር ዳር እና የአካባቢው ፍትህ ፈላጊ ወጣቶችም በአደባባይ ህግን እየጣሱ እና እያበላሹ ያሉ አፋኞችን በማውገዝ በሰባታሚት ማ/ቤት በር አካባቢ እየተጠባበቁ ይገኛሉ። ጉዳዩ በአፋኞች ህገ ወጥ አካሄድ ምክንያት እየታወቀም ቢሆን ለበጎ ነው በሚል፣ ግድ የለም ነገሩን በእነሱ ቦታ ሆነን እንየው በማለት በሀገር ሽማግሌዎችና በሀይማኖት አባቶች ጣልቃ ገብነት እየተከናወነ መሆኑ ይታወቃል። በተያያዘ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር በፋኖ ላይ የሚደረግ ተደጋጋሚ የሆነ ህገ ወጥ አፈና እና ማዋከብ እጅግ እንዳስቆጣው በመግለጽ ትግሉን እስከ ቀራኒዮ ከፍታ እንደሚያስቀጥል በመግለጫው አስታውቋል። ፎቶ_ያሬድ አላዩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply